በሰሞኑ የህወሓት መግለጫዎች ላይ የምሁራን ትችት
ማክሰኞ፣ መስከረም 26 2013ማስታወቂያ
የትግራይ ክልል ገዥ ፓርቲ ህዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ ፣ህወሓት፣የኢትዮጵያ ፌደራል መንግስት የሚያወጣቸው ሕጎች፣ ትዕዛዞችና ውሳኔዎች ከትናንት አንስቶ ተቀባይነት አይኖራቸውም ማለቱን ዶቼቬለ ያነጋገራቸው የአማራ ክልል ባለሥልጣን እና ምሁራን ተቹ። አስተያየት ሰጭዎቹ እንዳሉት በኮሮና ምክንያት የተራዘመው ምርጫ እስኪካሄድ ድረስ አሁን ኢትዮጵያን የሚያስተዳድረው መንግሥት ሕጋዊ ነው።ሥልጣኑም የተራዘመለት በሕጋዊ መንገድ መሆኑን አስረድተዋል።የትግራይ ክልልና የፌደራል መንግሥት ግንኙነት ተቋርጦ መቆየቱን ያስታወሱት አንድ ምሁር ደግሞ ሁለቱን የሚያገናኛቸው የበጀት ጉዳይ ሊያወዛግብ እንደሚችል ግምታቸውን ሰንዝረዋል።ያነጋገራቸው አለምነው መኮንን ከባህርዳር ዝርዝሩን ልኮልናል።
አለምነው መኮንን
ኂሩት መለሰ
ነጋሽ መሐመድ