1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

በሰሜን ሸዋ 50 ሺህ ሰዎች መፈናቀላቸው

ረቡዕ፣ ሚያዝያ 13 2013

በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ እና የኦሮሞ ልዩ ዞን አዋሳን አከባቢዎች በተፈጠረ ግኝት 50 ሺህ ሰዎች መፈናቀላቸውን የብሔራዊ አደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን አስታወቀ። የመጀመሪያ ደረጃ ድጋፍም ለተፈናቃዮቹ መደረጉን አመልክተዋል።

https://p.dw.com/p/3sKlz
Karte Sodo Ethiopia ENG

«የመጀመሪያ ደረጃ ድጋፍ ለተፈናቃዮች መድረሱ»

በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ እና የኦሮሞ ልዩ ዞን አዋሳን አከባቢዎች በተፈጠረ ግኝት 50 ሺህ ሰዎች መፈናቀላቸውን የብሔራዊ አደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን አስታወቀ። የኮሚሽኑ የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር አቶ ደበበ ዘውዴ ለዶይቼ ቬለ እንዳሉት ለተፈናቃዮች 3 ሺህ ኩንታል ስንዴ እና ሌሎች የመጀመሪያ ደረጃ የድጋፍ ቁሳቁስ ወደ ስፍራው ተልኳል። ለሰብዓዊ ቀውሱ ድጋፍ የአስቸኳይ ጊዜ ምላሽ ማስተባበሪያ ማዕከል ተቋቁሞ በቀጣይ የጉዳቱ መጠን እና ስፋት ተጠንቶ ድጋፉ እንደሚቀጥልም ተነግሯል። ዶይቼ ቬለ በአከባቢው የተከሰተው አለመረጋጋት ያስከተለው ቀውስ ላይ ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት ወደኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን እና ሰላም ሚኒስቴር የሥራ ኃላፊዎች  ያደረገው የስልክ ጥሪ እና የጽሁፍ መልእክቶች ምላሽ አላገኙም።

ሥዩም ጌቱ 

ሸዋዬ ለገሠ

እሸቴ በቀለ