1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

በርካታ በረራዎችን ያስተጓጎለዉ የአዲስ አበባዉ ጉም 

ረቡዕ፣ ሐምሌ 29 2012

አዲስ አበባን የሸፈነዉ ጉም በርካታ የአሃገር ዉስጥ እና የዉጭ ሃገር በረራዎችን ማስተጓጎሉ ተገለፀ። የአዲስ አበባዉ ወኪላችን ዮሃንስ ገብረግዚአብሔር ከአዲስ አበባ በላክልን ዘገባ አዲስ አበባ ላይ ወርዶ የነበረዉ እይታን ይከለክል የነበረዉ ጉም ከ 20 በላይ በራራዎችን አሰርዞአል አልያም አዘግይቶአል።

https://p.dw.com/p/3gSnq
Äthiopien Smoke in Addis Abeba
ምስል DW/Y. Geberegziabher

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ይቅርታ ጠይቆአል

አዲስ አበባን የሸፈነዉ ጉም በርካታ የአሃገር ዉስጥ እና የዉጭ ሃገር በረራዎችን ማስተጓጎሉ ተገለፀ። የአዲስ አበባዉ ወኪላችን ዮሃንስ ገብረግዚአብሔር ከአዲስ አበባ በላክልን ዘገባ አዲስ አበባ ላይ ወርዶ የነበረዉ እይታን ይከለክል የነበረዉ ጉም ከ 20 በላይ በራራዎችን አሰርዞአል አልያም አዘግይቶአል። ከአዲስ አበባ ወደ ኢትዮጵያ ሌሎች ክፍሎች ለመብረር ወደ አዲስ አበባ ቦሌ አዉሮፕላን ጣብያ የመጡ ደንበኞች ለመጓዝ አዉሮፕላን ሲጠብቁ ከ ስድስትና ሰባት ሰዓታት በላይ ወስዶባቸዋል። ምግብና የመጠጥ ዉኃ ሳያገኙ እንጓዛለን ብለዉ አዉሮፕላን ሲጠባበቁ ለዋሉ ደንበኞች ሁሉ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ይቅርታን ጠይቆአል። 

Ethiopian Air Lines
ምስል Ethiopian Air Lines

ዮሃንስ ገብረግዚአብሔር 
አዜብ ታደሰ 
ነጋሽ መሐመድ