1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል
ኤኮኖሚ

በሞባይል ስልክ ግብይት በኢትዮጵያ 

ረቡዕ፣ መስከረም 6 2013

በበርካታ የአፍሪቃ ሃገሮች በተንቀሳቃሽ ስልክ መገበያየት እየተለመደ ሆንዋል። መገበያያ ገንዘብን በኪስ ከመያዝ በገበያ ቦታ አልያም ለሌሎች ክፍያ ለሚያስፈልጋቸዉ ነገሮች ሁሉ በሞባይል መገበያየት ገንዘብን ከማቆሸሽ ብሎም የተለያዩ በሽታዎች በቀላሉ እንዳይሰራጩ ጥሩ መፍትሄ መሆኑ እንደታመነበት በለሞያዎች ይናገራሉ።

https://p.dw.com/p/3iXyN
Äthiopien Mobiler Geldservice
ምስል DW/M. Gerth-Niculescu

በሞባይል ግብይት ፈጣንና ከንክኪ የፀዳ ነዉ

 

በበርካታ የአፍሪቃ ሃገሮች በተንቀሳቃሽ ስልክ መገበያየት እየተለመደ ሆንዋል። መገበያያ ገንዘብን በኪስ ከመያዝ በገበያ ቦታ አልያም ለሌሎች ክፍያ ለሚያስፈልጋቸዉ ነገሮች ሁሉ በሞባይል መገበያየት ገንዘብን ከማቆሸሽ ብሎም የተለያዩ በሽታዎች በቀላሉ እንዳይሰራጩ ጥሩ መፍትሄ መሆኑ እንደታመነበት በለሞያዎች ይናገራሉ። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ኢትዮጵያ ዉስጥም በተንቀሳቃሽ ስልክ ክፍያን ማካሄድ እየተለመደ ነዉ። በእጅ ስልክ መገበያየት  በተለይ በሶማሌ ክልል ኮሮና ወረርሽኝን ለመከላከል ዋንኛ መፍትሄ ነዉ በመባሉ እየተጠናከረ ነዉ ተብሎአል።  የዶቼ ቬለዋ ማርያ ጌርት ኒኩልየሱስ በጅጅጋ ከተማ በሞባይል ስልክ ግብይትን ቃኝታ የዘገበችዉን የበርሊኑ ወኪላችን ያቀርበዋል። 

ይልማ ኃይለሚካኤል 
አዜብ ታደሰ