1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

በምዕራብ ኢትዮጵያ ከ20 በላይ ሰዎች ተገደሉ

ሰኞ፣ ሚያዝያ 25 2013

ባለፈው አርብ ከአሶሳ ከተማ ወደ መተከል ዞን  ሲሄድ የነበሩት ከሁለት በላይ ተሸርካሪዎች ላይ  በደረሰው ጥቃትም የክልሉ ልዩ ፖሊስን ጨምሮ የሰዎች ህይወት ማለፉን ከጥቃቱ የተረፉ ሰዎች በስልክ ለዲዳቢሊው ገልጸዋል፡፡ ጠዋት ሶስት አአካባቢ በመተክል ዞን ጉባ ወረዳ  ማንጎ በተባለ ቀበለ ሲደርሱ  በተከፈተው ተኩስ ነው የሰዎች ህወት ያፈው።

https://p.dw.com/p/3stKe
Äthiopien Benishangul Region, Stadt  Metekel
ምስል Negassa Dessakegen/DW

በምዕራብ ኢትዮጵያ ከ20 በላይ ሰዎች በታጣቂዎች ተገደሉ

ባለፈው አርብ ሚያዚያ 22/2013 ዓ.ም ከአሶሳ ወደ መተከል  እንዲሁም ከቡሬ ወደ ነቀምቴ መስመር ሲጓዙ በነበሩ ተሸከርካሪዎች ላይ ታጠቂዎች ጥቃት ማድረሳቸውን የአካቢቢው ነዋሪዎች ተናገዋል፡፡ በሁለቱም ስፋራዎች በደረሱት ጥቃቶች  20  በላይ ሰዎች ህይወት ማለፉን ከጥቃቱ የተረፉ ሰዎች አስታወቋል።  የሆሮ ጉደሩ ወለጋ ዞን አስተዳዳሪ ጥቃት መፈሙን ያረጋገጡ ሲሆን የጉዳት መጠኑን አልገለጹ፡፡ የሆሮ ጉዱሩ ወለጋ ዞን ፖሊስ አዛዥ ኮማንደር ብርሃኑ የባሳ 15 ሰዎች  በቡሬ መስመር ህይወት ማለፉን መናገራውን ከኢትቪ ያገኘው መረጃ ያመልክታል፡፡ በመተከል ዞን በጉባ ወረዳ በደረሰው ጥቃት ደግሞ የመንገሰት ጸጥታ ሐይሎች  ላይም ጉዳት መድረሱን ተግልጿል፡፡ ከመተከል ዞን ኮማንድ ፖስት/ አስቸኳይ ጊዜ አስተዳደሩና የጸጥታ ዘርፍን ከሚመሩ የስራ ሃላፊዎች በስልክ መረጃ ለማግኘት ያደረግነው ጥረት አልተሳካም፡፡

በምእራብ ኢትዮጵያ በሚገኙ የተለያዩ ስፋራዎች በዜጎች ላይ በሚደርሱ ተደጋጋሚ ጥቃቶች ምክንያት የበርካቶች ህይወት ሲያልፍ እና ሌሎች ደግሞ ሲፈናቀሉ መስማት እየተለመደ ሆነዋል፡፡ ባለፈው አርብ ከአሶሳ ከተማ ወደ መተከል ዞን  ሲሄድ የነበሩት ከሁለት በላይ ተሸርካሪዎች ላይ  በደረሰው ጥቃትም የክልሉ ልዩ ፖሊስን ጨምሮ የሰዎች ህይወት ማለፉን ከጥቃቱ የተረፉ ሰዎች በስልክ ለዲዳቢሊው ገልጸዋል፡፡ ጠዋት ሶስት አአካባቢ በመተክል ዞን ጉባ ወረዳ  ማንጎ በተባለ ቀበለ ሲደርሱ  በተከፈተው ተኩስ ነው የሰዎች ህወት ያፈው። ከተሳፋሪዎቹ መካከል ተማሪዎች እና የጤና ባለሙያዎች ይገኙበታል። ሰዎቹ በተለያዩ መኪኖች ተሳፋረው ወደ ግልገል በለስ እና ማንኩሽ እያቀኑ እንደነበር ተናግረዋል።

ከመተከል ዞን ኮማንድ ፖስት የስራ ሀላፊዎች በስልክ  መረጃ ለማግኘት ጥረት ቢናደርገም ስልክ ባለማንሳታቸው ሀሳባቸውን ማካተት አልተሳከም፡፡

በተመሳሰይ ባለፈው አርብ ከምዕራብ ጎጃም ቡሬ ወደ ነቀምቴ መስመር ሲሄድ ነበር በተባለው ተሸርካሪ ላይ በደረሰው ጥቃት እንደዚሁ የሰዎች ህይወት ማለፉን የአካባቢው ነዋሪዎች ተናግረዋል፡፡ አንድ ስማቸው እንዲገልጸ ያልፈለጉ በአሙሩ ወረዳ አጋማሳ በሚባል ከተማ ነዋሪ እንደነገሩን  ከሞቱት በተጨማሪ  ሰዎች መታገታቸውን ጠቁመዋል፡፡ በመኪናው ከመጡት መንገደኞች መካከከል የተወሰኑት ወደ ጊዳ አያና ወረዳ መግባታውንም አክልዋል፡፡

የሆሮ ጉደሩ ወለጋ ዞን ዋና አስተዳዳር አቶ በቀሌ  ደቻሳ በተሸከርካሪ ላይ ጥቃት መፈጸሙን ያረጋገጡ ሲሆን  የደረሰው የጉዳት መጠን አልገለጹም፡፡ የዞኑ የፓሊስ አዛዥ ኮማንደር ብርሀኑ የባሳ ከቡሬ ወደ ነቀምት ሲያቀና በነበረ መኪና ውስጥ የነበሩ በርካታ ሰዎች ህይወት ስለማለፉ ለኢቲቪ ተናረዋል፡፡  ሌሎች መንገደኞችም መታገታቸውን ጠቁመዋል፡፡

ከመስከረም ወር ወዲህ በምእራብ ኢትጱያ የሚገኙ የተለያዩ ስረዎች በተሸከርካሪዎች ላይ በሚፈጸሙት ጥቃቶች ምክንያት በርካታ ሰዎች ህይወት እያለፈ ይገኛል፡፡