1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

በመንገድ ዳር ቦምብ ፍንዳታ 10 ሰዎች ሞቱ 

ረቡዕ፣ ታኅሣሥ 10 2011

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ከአሶሳ ቶንጎ ወደተባለች አነስተኛ የገጠር ከተማ መንገደኞች አሳፍሮ ይጓዝ የነበረ ተሽከርካሪ ከመንገድ ዳር በተቀበረ ፈንጂ በደረሰበት አደጋ ቢያንስ አስር ሰዎች ሞቱ። በአደጋው የቆሰሉ በርካታ ሰዎች በምዕራብ ወለጋ ዞን በሚገኘው ቤጊ በተባለች ከተማ በሚገኝ የሕክምና ማዕከል እገዛ እየተደረገላቸው ይገኛል።

https://p.dw.com/p/3AOvL
Asosa, West-Äthiopien und Hauptstadt der Region Benishangul-Gumuz
ምስል privat

ተሽከርካሪው 18 ሰዎች አሳፍሮ ይጓዝ ነበር

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ከአሶሳ ቶንጎ ወደተባለች አነስተኛ የገጠር ከተማ መንገደኞች አሳፍሮ ይጓዝ የነበረ ተሽከርካሪ ከመንገድ ዳር በተቀበረ ፈንጂ በደረሰበት አደጋ ቢያንስ አስር ሰዎች ሞቱ። በአደጋው የቆሰሉ በርካታ ሰዎች በምዕራብ ወለጋ ዞን በሚገኘው ቤጊ በተባለች ከተማ በሚገኝ የሕክምና ማዕከል እገዛ እየተደረገላቸው ይገኛል። የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ሰይፈዲን ሐሩን ተሽከርካሪው 18 ሰዎች አሳፍሮ ይጓዝ እንደነበር አረጋግጠዋል። ነጋሽ መሐመድ በአሶሳ ከተማ የሚገኙ አንድ ሰው ስለ ጉዳዩ በስልክ መረጃ ጠይቋል። 
ነጋሽ መሐመድ
እሸቴ በቀለ