1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

በመተከል የታጣቂዎች ጥቃት

ሰኞ፣ ጥቅምት 30 2013

ባለፈው ቅዳሜ በቤቢሻንጉል ጉሙዝ ክልል መተከል ዞን ታጣቂዎች በፈጸሙት የደፈጣ ጥቃት ፖሊሶች ተገድለው ስድስት የሕክምና ባለሙያዎች መታገታቸውን የዐይን እማኞች ተናገሩ። የክልሉ ፖሊስ እንዳለው በደፈጣ ጥቃቱ ሶስት ፖሊሶች ተገድለዋል። የታገቱት ሰዎች ቁጥር 12 ሳይደርስ አይቀርም።

https://p.dw.com/p/3l3pi
Karte Äthiopien Metekel EN

በመተከል ሶስት ፖሊሶች ተገድለው ሰዎች መታገታቸውን የክልሉ ፖሊስ አስታወቀ

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መተከል ዞን ዳንጉር ወረዳ የጤና ባለሙያዎች ጨምሮ ስድስት ሰዎች በታጣቂዎች መታገታቸውን የአካባቢው ነዋሪዎች አስታወቁ።  የታገቱት  የጤና ባለሙያዎች  በዳንጉር ወረዳ የጉብላክ ቀበሌ ጤና ጣቢያ የህክምና ባለሙያዎች ሲሆኑ ባለፈው ቅዳሜ ከጉብላክ ቀበሌ በቅርብ ርቀት ላይ በሚገኘው የዳንጉር ወረዳ ከተማ ወደ ሆነው ማምቡክ እያቀኑ ባሉበት ሰዓት መታገታቸውን ተናግረዋል። ከታገቱት መካከል አምስቱ ሴቶች ናቸው ተብለዋ። የቤኒሻንል ጉሙዝ ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር አብዱልአዚም ሙሐመድ  በበኩላቸው ጉዳዩን እየተከታተሉ እንደሚገኙ አስታውቀዋል። የታገቱት ሰዎችም 12 ይደርሳሉ ብለዋል።

በመተከል ዞን የተለያዩ ወረዳዎች ተፈጥሮ በነበረው ተደጋጋሚ ግጭት ምክንያት በኮማንድ ፖስት እንዲጠበቁ ከተወሰኑ ወረዳዎች መካከል ዳንጉር ወረዳ አንዱ ነው።  ከትናንት በስቲያ ቅዳሜ በአካባቢው የጸጥታ ሀይሎችን ጨምሮ  ሰላማዊ ሰዎች መታገታቸውን ነዋሪዎች ተናግረዋል። በወረዳዋ ስር የሚገኘው ጉብላክ የተባለ ቀበሌ ጤና ጣቢያ የሚሰሩ  ባለሙያዎችም ወደ ማምበኩክ ከተማ በፖሊሶች ታጅበው እያቀኑ ባለቡት ሰዓት ታጣቂዎች በደፈጣ ተኩስ በመክፈት አንድ ፖሊስ ሲቆስል  ሰድስት የሚደረስ ባሙያዎችን ጨምሮ ፖሊሶችን መታገታቸውን አብራርተዋል። ዛሬ ጠዋትም በማምቡክ ደግሞ ከተማ የታገቱት ይለቀቁ በማለት ነዋሪው  ጥያቄውን ሲያቀርብ እንደነበር እና የጸጥታ ችግርም ተፈጥሮ እስከ አራት ሰዓት ድረስ በከተማ ተኩስ እንደነበር ተገልጸዋል። 

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር አብዱልአዚም ሞሐመድ በስልክ እንደተናሩት በዳንጉር ወረዳ ባለፈው ቅዳሜ ሰዎች መታገታቸውን እና ሰዎቹን ለማስለቀቅ  ኦፕሬሽን እያደረጉ እንደሚገኙ ተናግረዋል። በዳንጉር ወረዳ ከምትገኘው ማምቡክ ከተማ በ35 ኪ.ሜ ርቀት ላይ በምትገኝዋ ጉብላክ ቀበሌ በዕለቱ ሶስት ጸጥታ ሀይሎች ሰዎችን አጅበው ሲንቀሳቀሱ በታጣቂዎች መገደላቸውን ኮሚሽነር አብዱልአዚም አመልክተዋል። ከባለሞያዎቹ በተጨማሪም ሁለት ፖሊሶች  መታገታቸውን አክለዋል።  ዛሬ በማምቡክ ከተማ የነበረው ታቃውሞም ከዚሁ ጉዳይ ጋር የሚገናኝና የታገቱትን አስለቅቁ የሚል ነበር ብለዋል።   የታገቱት ሰዎች ቁጥርን በተመለከተም እስካሁን በኮሚሽኑ መረጃ መሰረት 12 ሲሆኑ፤ የተለቀቀ አንድ ሰው ብቻ መሆኑንን ኮሚሽነሩ ገልጸዋል።

ከባለፈው መስከረም 2013 ዓ.ም አንስቶ ለሶስት ወራት በኮማንድ ፖስት እንዲመራ የተወሰነው መተከል ዞን ውስጥ ተደጋጋሚ ጥቃቶች እየደረሱ ይገኛሉ። በዞኑ ከዚህ ቀደም የተፈጠሩ የጸጥታ ቸግሮችን ለመቅረፍ ኃላፊነታቸውን አልተወጡም የተባሉ ከ40 በላይ አመራሮች ከስራቸው እንዲነሱ ተደርገዋል። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ደግሞ የዞኑንን የጸጥታ ችግሮችን በኮማንድ ፖስት ብቻ መፍታት አይቻል በማለት በዞኑ ስር ከሚገኙት ሰባት ወረዳዎች የተውጣጡ ሚሊሻዎች ተመልምለው ስልጠና መውሰዳቸውን በጸጥታ ማስከበር ስራ እንደሚሰማሩ መገለጹም የሚታወስ ነው። በመተከል ዞን ዳንጉር ወረዳ በንጹሐን ዜጎች ላይ ጥቃት ሲያርሱ የነበሩ 16 ሽፍቶች መደምሰስአቸውን ዛሬ ከሰዓት የቤኒሻንል ጉሙዝ ክልል ኮሙኒኬሽ ጉዳዩች ጽህፈት ቤት በፌስቡክ ገጹ ይፋ አድርጓል። 

ነጋሳ ደሳለኝ

እሸቴ በቀለ
ሸዋዬ ለገሠ