1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

በሐረር የራስ መኮንን ሐዉልት በተቃዋሚዎች ፈረሰ

ማክሰኞ፣ ሰኔ 23 2012

በአርቲስ ሃጫሉ ሁንዴሳን የግፍ ግድያ ተከትሎ በጅማ ከተማ ጎዳናዎች ተሽከርካሪዎች ተቃጥለው ሆቴሎች መሰባበራቸው ተነግሮአል። በአዳማ የከንቲባ ጽ/ ቤትን ጨምሮ የመንግሥት መሥሪያ ቤቶች በግድያው የተቆጡ ሰልፈኞች የጥቃት ዒላማም ሆነዋል። በአዳማም በነበረዉ ተቃዉሞ ላይ በተቀሰቀሰ ግጭት ሦስት ሰዎች መሞታቸዉ ነዉ የተነገረዉ።

https://p.dw.com/p/3ebDG
Ras Makonnens Statue wurde von Demonstranten abgerissen
ምስል Privat

በድሬደዋ ዙርያም ተኩስ ይሰማ ነበር

በአርቲስ ሃጫሉ ሁንዴሳን የግፍ ግድያ ተከትሎ በጅማ ከተማ ጎዳናዎች ተሽከርካሪዎች ተቃጥለው ሆቴሎች መሰባበራቸው ተነግሮአል። በአዳማ የከንቲባ ጽ/ ቤትን ጨምሮ የመንግሥት መሥሪያ ቤቶች በግድያው የተቆጡ ሰልፈኞች የጥቃት ዒላማም ሆነዋል። በአዳማም በነበረዉ ተቃዉሞ ላይ በተቀሰቀሰ ግጭት ሦስት ሰዎች መሞታቸዉ ነዉ የተነገረዉ። በድሪደዋ ዙርያ እና በሐረርም ከፍተኛ ተቃዉሞና ጥቃት የንብረት ዉድመት ነበር። በሃረር አደባባይ የነበረዉ የራስ መኮንን ሐዉልት በተቃዋሚ ወጣቶች ፈርሶአል። የድሪደዋዉን ወኪላችንን ስለሁኔታዉ ጠይቀነዉ ነበር። 

መሳይ ተክሉን

አዜብ ታደሰ

እሸቴ በቀለ