1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

በህወሓት ስር የምትገኘዉ የላሊበላ ወቅታዊ ሁኔታ

ማክሰኞ፣ መስከረም 11 2014

በዓለም የቅርስ የተያዙ አብያተ ክርስትያናት የሚገኙባት ላሊበላ ከተማ በህወሓት እጅ ሥር የገባችዉ ሐምሌ 29 እለተ ሃሙስ ቀትር ላይ ነበር። ላሊበላ ወደ 700 ካህናቶች ይገኛሉ፤ በጣም በሚያሳዝን ሁኔታ ላይ ይገኛሉ። የላሊበላ ችግር የጀመረዉ ህወሓት ከገባ በኋላ ሳይሆን ኮሮና በዓለማችን ከተስፋፋ ወዲህ ጀምሮ ነዉ። አሁን ግን ችግሩ ተባብሶአል።

https://p.dw.com/p/40bpc
Äthiopien Lalibela | Orthodoxe unterirdische monolithische Kirche Bete Giyorgis
ምስል picture alliance / Sergi Reboredo

ወጣቱ ወደ ባህርዳር እየተሰደደ ነዉ

የዓለም ቅርስ ሆነው የተመዘገቡ የአስደናቂ ውቅር አብያተ ክርስትያናት ባለቤት የሆነችው ላሊበላ ከተማ እንዴት ከረመች ? በሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት መቀስቀስን ተከትሎ በህወሓት ታጣቂ ኃይሎች ቁጥጥር ሥር እንደገባች የተነገረው ላሊበላ ከተማ፣ ሕዝቧ እና ቅርሶቿ አሁን በምን ሁኔታ ይገኛሉ ? ከሁለት ቀናት በፊት ከተማዋን ለቅቆ የወጣ አንድ ወጣትን አነጋግረናል።

Äthiopien Lalibela
ምስል Sergi Reboredo/picture alliance

 

ሰለሞን ሙጬ 

አዜብ ታደሰ 

ማንተጋፍቶት ስለሺ