1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

በሃዋሳ የተፈናቀሉትን መልሶ ማቋቋም 

Merga Yonas Bula
ሐሙስ፣ ሐምሌ 26 2010

የደቡብ ብሔር፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል በቅርብ በሃዋሳ ከተማ በተፈጠረዉ ግጭት ምክንያት ከቀያቸዉ የተፈናቀሉ ወገኖችን ከዛሬ ጀምሮ ወደቤታቸዉ እንደሚመለሱ ማሳወቁን የአገር ዉስጥ መገናኛ ብዙሃን ዘገባ ያመለክታል። ተፈናቃዮቹን መልሶ ለማቋቋምም መንግሥት ጊዚያዊ የገንዘብ ርዳታ እንደሚያደርግላቸዉ ገልጿል።

https://p.dw.com/p/32Wjh
Karte Sodo Ethiopia ENG

Resettling the displaced in Hawassa - MP3-Stereo

ከአንድ ወር በፊት በሃዋሳ ከተማ በተፈጠረዉ ግጭት ምክንያት 12,000 ሰዎች ከቀያቸዉ መፈናቀላቸዉን የደቡብ ብሔር፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል የኮሙኒኬሼብ ጉዳዮች ቢሮ ኃላፊ አቶ ሰለሞን ኃይሉ ለዶይቼ ቬሌ ገልጸዋል።

እነዚህ ተፈናቃዮች ከዛሬ ጀምሮ ወደየቀያቸዉ እንደሚመለሱምና ለቤት ክራይ እንዲሁም ለቀለብ ድጋፍ እንደሚደረግላቸዉም አመልክተዋል። ተፈናቃዮቹ ከተመለሱ በኋላ በዘላቂነት እንዴት መኖር ይችላሉ የሚለዉ ላይ ዉይይት መደረጉንም ጠቅሰዋል።

የግጭቱ ሰለባ የነበረዉ አሁን ወደ ቤተሰቦቹ የተመለሰ ስሙ እንዳይጠቀስ የፈለገ በሃዋሳ የታቦር ክፍለ ከተማ ነዋሪ ክልሉ የሚያደርገዉን ርዳታ በበጎ ይመለከታል። ግን መንግሥት ዘላቅ መፍትሄ ለማምጣት በሰላም ላይ መስራት አለበት ይላል።

የደቡብ ብሔር፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል የኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ኃላፊ አቶ ሶሎሞን ኃይሉ ተፈናቃዮቹ ዛሬ ወደ ቤታቸዉ ይመለሳሉ  ቢሉም እስከ እኩለ ቀን ድረስ ምንም እንዳልተመለከቱ ሌላ የሃዋሳ ከተማ ነዋሪ ይናገራሉ።

በክልሉ ከተሞች ማለት፣ በሃዋሳ ፣በወላይታ ሶዶና በዉልቂጤ ብሔርን መሠረት ያደረገ ግጭት ምክንያት ለሰው ሕይወት መጥፋት፤ ለሺህዎች መፈናቀልና ለንብረት ውድመት ምክንያት ሆኗል።

መርጋ ዮናስ

ሸዋዬ ለገሰ