በሀዋሳ በጦርነት ለተፈናቀሉ ርዳታ ተሰበሰበ
ሰኞ፣ ኅዳር 20 2014ማስታወቂያ
በኢትዮጵያ ሰሜናዊ ክፍል እየተካሄድ የሚገኘውን ጦርነት ተከትሎ ለተፈናቀሉ ወገኖች በሀገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎቸ የሚገኙ ነዋሪዎች ድጋፍ እያደረጉ ይገኛሉ። የሀዋሳ ከተማ የተለያዩ የማኅበረሰብ ክፍሎችም በጦርነቱ ለተፈናቀሉ ዜጎች ከ70 ሚሊየን ብር በላይ ድጋፍ አሰባስበዋል።
ዛሬ በተካሄደው በድጋፍ ሥነ-ስርዓት ላይ የተገኙት የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ረዳት ፕሮፌሰር ፀጋዬ ቱኬ ኢትዮጵያዊያን አገራቸው ፈርሶባቸው እንደተቸገሩ ሰዎች እንዳንሆን መተባበር ይኖርብናል ብለዋል።
ሸዋንግዛዉ ወጋየሁ
አዜብ ታደሰ
ነጋሽ መሐመድ