1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ቃለ-ምልልስ ከአቶ በቀለ ገርባ ልጅ ተማሪ ሳሙኤል በቀለ ጋር 

ዓርብ፣ ሐምሌ 10 2012

ሳሙኤል  በማዕከሉ በአጠቃላይ አቶ ጃወር መሐመድ እና አቶ በቀለ ገርባን ጨምሮ 36 ሰዎች መያዛቸዉን ተናግሮአል።እነርሱን ጨምሮ በወቅቱ  ከተያዙት 36 ሰዎች መካከል ሦስቱ ብቻ መፈታታቸውን የ23 ዓመቱ ሳሙኤል በቀለ ለዶቼቬለ ተናግሯል።ወጣት ሳሙኤል በቁጥጥር ስር እንደዋሉ፤አያያዙ ጥሩ እንዳልነበር ምግብም ለ36 ሰዓት አለማግኘታቸዉን ተናግሮአል።

https://p.dw.com/p/3fVr5
Äthiopien Militär Pick-up Truck in Addis Abeba
ምስል Reuters/T. Negen

በቁጥጥር ሥር እንደዋልን አያያዙ ጥሩ አልነበረም፤ ምግብም ለ36 ሰዓት አላገኘንም

የአሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ  ምክትል ሊቀመንበር  የአቶ በቀለ ገርባ ሁለት ልጆችና አንድ የአክስታቸው ልጅ ትናንት በዋስ ተለቀዋል።ልጆቻቸው ቦንቱ በቀለ እና ሳሙኤል በቀለ ከሁለት ሳምንት በፊት የአርቲስት ሃጫሉ ሁንዴሳ አስከሬን ከቡራዩ ወደ አዲስ አበባ ተመልሶ ኦሮሞ የባህል ማዕከል ከደረሰ በኋላ ነበር ከአባታቸው ጋር በቁጥጥር ስር የዋሉት። የኦሮሞ ባህል ማዕከል በቁጥጥር ስር መዋሉን የተናገረዉ የአቶ በቀለ ልጅ ፤ ሳሙኤል  በማዕከሉ በአጠቃላይ አቶ ጃወር መሐመድ እና አቶ በቀለ ገርባን ጨምሮ 36 ሰዎች መያዛቸዉን ተናግሮአል።እነርሱን ጨምሮ በወቅቱ  ከተያዙት 36 ሰዎች መካከል ሦስቱ ብቻ መፈታታቸውን የ23 ዓመቱ ሳሙኤል በቀለ ለዶቼቬለ ተናግሯል። ወጣት ሳሙኤል በቁጥጥር ስር እንደዋሉ ፤ አያያዙ ጥሩ እንዳልነበር ምግብም ለ36 ሰዓት አለማግኘታቸዉን ተናግሮአል። 

ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር


ኂሩት መለሰ
ነጋሽ መሐመድ