1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል
ሳይንስ

ቃለ-ምልልስ ከቤተልሔም ደሴ ጋር

ረቡዕ፣ ግንቦት 21 2011

በዶይቼ ቬለ (DW) በየዓመቱ በሚዘጋጀው ዓለም አቀፍ የመገናኛ ብዙሃን መድረክ ላይ የተመረጡ ባለሙያዎች ተሞክሮቻቸውን እንዲያጋሩ ይጋበዛሉ። ለሁለት ቀናት በተካሄደው እና ትላንት ግንቦት 21 በተጠናቀቀው የእዚህ ዓመት ዝግጅት ላይ በቁልፍ ተናጋሪነት ከተጋበዙት መካከል ኢትዮጵያዊቷ ወጣት የኮምፒውተር ባለሙያ ቤተልሔም ደሴ አንዷ ናት።

https://p.dw.com/p/3JS8a
19 | TV-Show | Arts on the Edge: Can AI be truly creative?
ምስል DW/R. Oberhammer

ቃለ-ምልልስ ከቤተልሔም ደሴ ጋር

የሐረር ልጅ ናት። የ20 ዓመት ወጣት።  የኮምፒዩተር ፕሮግራም መጻፍ (ኮዲንግን) ተክናበታለች። ከኮምፒውተር ጋር የተያያዙ ነገሮች መሥራት የጀመረችው ገና የ10 ዓመት አዳጊ እያለች ነው። እስካሁን አራት መተግበሪያዎችን (አፕልኬሽኖችን) ሠርታለች። ወጣቶች የቴክኖሎጂ እና የፈጠራ ሥራዎችን እንዲሠሩ የሚያበረታታ  «ሶልቭ ኢት» የተሰኘ ሀገር አቀፍ ውድድር ታስተባብራለች።  ለተወዳዳሪዎቹ እና ለሌሎች ወጣቶችም የኮምፕውተር ፕሮግራም መጻፍ (ኮዲንግ) ስልጠና ትሰጣለች። ቤተልሔም ደሴ ትባላለች። 

19 | TV-Show | Arts on the Edge: Can AI be truly creative?
ምስል DW/R. Oberhammer

ገና በለጋ ዕድሜዋ ዕውቅና እና ዝና ያተረፈችው ቤተልሔም ከተለያዩ አጋሮች ጋር በመተባበር ወጣቶች የኮምፒውተር ፕሮግራም እና የቴክኖሎጂ ዕውቀት እንዲገበዩ እያደረገች ትገኛለች። ኢትዮጵያውያን ወጣቶች የፈጠራ ክህሎታቸው እንዲዳብር እንደምትሻ የምትናገረው ቤተልሔም እያከናወነቻቸው ስላለቻቸው ጉዳዮች ከዶይቼ ቬለ ለቀረቡላት ጥያቄዎች ምላሽ ሰጥታለች። ቤተልሔም ከዓመታት በፊት ስለሰራቸው መተግበሪያ፣ በአስተባባሪነት ስለምትመራው የኮምፒውተር ቴክኖሎጂ እና የፈጠራ ውድድር እንደዚሁም ለወጣቶች ስለምትሰጣቸው ስልጠናዎች አብራርታለች። 

ሙሉ ቃለ ምልልስ ለማድመጥ የድምጽ ማዕቀፉን ይጫኑ። 

ተስፋለም ወልደየስ 

ሸዋዬ ለገሠ