1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ቃለ መጠይቅ፣ ዉጠረትና የሰላም ድርድር በኢትዮጵያ

ነጋሽ መሐመድ
ማክሰኞ፣ ግንቦት 1 2015

የኢትዮጵያ መንግስት በአማራ ክልል የናረዉን ዉጥረት ለማስተንፈስ በኃይልም፣በዛችም፣በሕግም እየተጫነ፣ ኦሮሚያ ዉስጥ ከሸመቀዉ ከኦሮሞ ነፃ አዉጪ ሰራዊት (ኦነሰ) ጋር ድርድር ጀምሯል

https://p.dw.com/p/4R6cy
Bayisa Wak-Woya | ehemaliger UN Repräsentant
ምስል Privat

ከአቶ ባይሳ ዋቅ ወያ ጋር የተደረገ ቃለ መጠይቅ

 

የኢትዮጵያ ፈደራዊ መንግስትና ህዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) ከ6 ወራት በፊት ያደረጉት ስምምነት ገቢራዊነት አልፎ አልፎ ጥያቄ ቢነሳበትም በአብዛኛዉ ገቢር እየሆነ ነዉ።የተለያዩ መንግስታትም የስምነቱን ገቢራዊነት እያደነቁ ለቀድሞ ተፋላሚ ኃይላት ድጋፋቸዉን እየሰጡ ነዉ።

ይሁንና በጦርነቱ ወቅት ከፌደራሉ መንግስት ጦር ጋር አብረዉ ህወሐትን ሲወጉ በነበሩት በአማራ ክልል ልዩ ልዩ ኃይላት ዘንድ የተፈጠረዉ ቅሬታ እልባት አላገኘም።የኢትዮጵያ መንግስት «የክልሎችን ልዩ ኃይላት ዳግም ለማደራጀት» በሚል ዉሳኔ የአማራ ክልል ልዩ ኃይልን ትጥቅ ማስፈታት ከጀመረ ወዲሕ ደግሞ ቅሬታዉ ተባብሶ ወደ ግጭትና  ዉጥረት ንሯል።

ማሕደረ ዜና፣ ኢትዮጵያ የስምምነት ማግስት ጠብና ዉጥረት

የኢትዮጵያ መንግስት በአማራ ክልል የናረዉን ዉጥረት ለማስተንፈስ በኃይልም፣በዛችም፣በሕግም እየተጫነ፣ ኦሮሚያ ዉስጥ ከሸመቀዉ ከኦሮሞ ነፃ አዉጪ ሰራዊት (ኦነሰ) ጋር ድርድር ጀምሯል።እስካለፈዉ ሳምንት ሮብ ድረስ ዛንዚባር-ታንዛኒያ ዉስጥ የተደረገዉ ድርድር ግን ያስገኘዉ ሁነኛ ዉጤት የለም።የሕግ ባለሙያና የቀድሞዉ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ባይሳ ዋቅወያ እንደሚሉት ግን ተደራዳሪዎች ለዘጠኝ ቀን መነጋገራቸዉና ወዲፊት ለመነጋገር መስማማታቸዉ ራሱ ጥሩ ስኬት ነዉ።ከአቶ ባይሳ ዋቅ ወያ ጋር ያደረግነዉ ሙሉ ቃለ መጠይቅ ተከታዩን ማገናኛ በመጫን ያድምጡ።

ነጋሽ መሐመድ

ሸዋዬ ለገሰ