1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ቃለ መጠይቅ ከ«አፋር ሕዝብ ፓርቲ» መሪ ጋር

ረቡዕ፣ መስከረም 18 2015

የጦርነት ሜዳ ከሆኑት ክልሎች አንዱ በሆነው የአፋር ክልል የሚንቀሳቀሰው «የአፋር ሕዝብ ፓርቲ» መሪ የሆኑት አቶ ሙሳ አደምን ሰሞኑን ብራስልስ በሥራ ጉብኝት ላይ በነበሩበት ወቅት ከዶይቸ ቬለ ጋር ቃለ መጠይቅ አድርገዋል። የፓለቲካ ፓርቲያቸው ጦርነቱ እንዲቆምና በኢትዮጵያ ሰላም እንዲሰፍን ምን እያደረገ ነው?

https://p.dw.com/p/4HTDY
DW-Interview mit Ato Mussa Adem, Präsident Afar Peoples Party
ምስል Gebeyaw Nigusie/DW

«የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነታችን በጣም አደጋ ላይ ነው»

በ2013 ዓ.ም ጥቅምት ወር ላይ የተጀመረው የፊደራል መንግስትና የሕዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ (ሕወሓት) ጦርነት  ወደ አማራና አፋር ክልሎች ተስፋፍቶ የበርካቶችን ሕይወት እየቀጠፈና በሚሊዮን የሚቆጠሩትን እያፈናቀለ አሁን ድረስ ዘልቋል። ለተወሰኑ ወራት ጋብ ብሎ የነበረው ጦርነት ባለፈው ነሐሴ ወር ሕወሓት በወሎ የቆቦ ግንባር ወረራ በማካሄድ ተጣሰ ከተባለ ወዲህ ዋግ ሁምራ፤ ሰሜን ወሎ፤ አፋር፤ ስሜን ጎንደርና ትግራይ በከፋ ጦርነት ውስጥ ናቸው። በተወሰኑ ቡድኖች የፖለቲካ ልዩነትና ፍላጎት ምክንያት የአንድ አገር ሕዝቦች ይህን ለመሰለ አስከፊ ጦርነት መዳረጋቸው ለብዙዎች እንቆቅልሽ ነው። የብራስልስ ወኪላችን ገበያው ንጉሤ የጦርነት ሜዳ ከሆኑት ክልሎች አንዱ በሆነው የአፋር ክልል የሚንቀሳቀሰው «የአፋር ሕዝብ ፓርቲ» መሪ የሆኑትን አቶ ሙሳ አደምን ሰሞኑን ብራስልስ በሥራ ጉብኝት ላይ በነበሩበት ወቅት አግኝቶ አነጋግሯቸዋል። የእናንተ የፓለቲካ ፓርቲ ጦርነቱ እንዲቆምና በዚህች አገር ሰላም እንዲሰፍን ምን እያደረገ ነው የሚለው ነበር የመጀመሪያ ጥያቄው።

ገበያው ንጉሤ

ማንተጋፍቶት ስለሺ

ታምራት ዲንሳ