1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ቀይ መስቀል በጦርነቱ የተጠፋፉትን ለማገናኘት እየሰራሁ ነው አለ

ማክሰኞ፣ ኅዳር 15 2013

በትግራይ ክልል በፌዴራል መንግስት እና በህወሃት ኃይሎች መካከል እየተደረገ ያለው  ጦርነት ከተጀመረ ወዲህ የስልክ እና ኢንተርኔት አገልግሎቶች በመቋረጣቸው በርካቶች  ወዳጆቻቸው ያሉበትን  ሁኔታ ማወቅ ባለመቻላቸው መጨነቃቸውን ተናግረዋል።

https://p.dw.com/p/3llPc
Äthiopien, Rotes Kreuz
ምስል DW/G. Tedla

የቀይ መስቀሉ በትግራይ ጦርነት የተጠፋፉ ቤተሰቦችን ሊያገናኝ ነው

የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማኅበር እና ዓለም አቀፉ የቀይ መስቀል ኮሚቴ በትግራይ ክልል የሚገኙ ነዋሪዎችን ደኅንነት በማጣራትና አድራሻቸውን በማፈላለግ ለወዳጅ ዘመዶቻቸው እያሳወቁ ነው።
ማንኛውም ሰው የቤተሰቡንና ወዳጅ ዘመዱን ደኅንነት ለማወቅ ለዚሁ ሲባል ወደተዘጋጁ የስልክ መስመሮች በመደወል እና በአካል ቀይ መስቀል ማኅበር ሄዶ በመመዝገብ መረጃ ከሰጠ በኃላ ሁለቱ ተቋሞች ተፈላጊዎችን መቀሌ በሚገኘው ጽህፈት ቤታቸው በኩል በማፈላለግ ያገኙትን ውጤት መልሰው ለጠያቂው ሰው እያሳወቁ እንደሚገኙ ገልጸዋል።
በትግራይ ክልል በፌዴራል መንግስት እና በህወሃት ኃይሎች መካከል እየተደረገ ያለው  ጦርነት ከተጀመረ ወዲህ የስልክ እና ኢንተርኔት አገልግሎቶች በመቋረጣቸው በርካቶች  ወዳጆቻቸው ያሉበትን  ሁኔታ ማወቅ ባለመቻላቸው መጨነቃቸውን ተናግረዋል።

ሰለሞን ሙጬ 

ታምራት ዲንሳ

ማንተጋፍቶት ስለሺ