1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ሶማልያዉያን ስደተኞችና የአሜሪካዉ ምርጫ

ማክሰኞ፣ ኅዳር 1 2013

የዩናይትድ ስቴትሱ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ የሶማልያ ስደተኞች ወደ ዩናይትድ ስቴትስ እንዳይገቡ ከከለከሉ አራት ዓመት ግድም በኋላ ዛሬ በአሜሪካ የፊታችን ማክሰኞ የሚካሄደዉ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ እና ዉጤቱ ጉዳዩን ሊቀይረዉ ይችላል የሚል ተስፋን ሰንቅዋል።

https://p.dw.com/p/3kgGa
Kenia Das Flüchtlingslager Dadaab
ምስል imago/Xinhua

የትራምፕ አለመመረጥ የሶማልያ ስደተኞችን አሜሪካ ይመልስ ይሆን?

የዩናይትድ ስቴትሱ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ የሶማልያ ስደተኞች ወደ ዩናይትድ ስቴትስ እንዳይገቡ ከከለከሉ አራት ዓመት ግድም በኋላ ዛሬ በአሜሪካ የፊታችን ማክሰኞ የሚካሄደዉ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ እና ዉጤቱ ጉዳዩን ሊቀይረዉ ይችላል የሚል ተስፋን ሰንቅዋል።

ፕሬዚዳንት ትራምፕ በጎርጎረሳዉያኑ 2016 ዓም ወደ ስልጣን ከመጡ ከጥቂት ጊዜያት ወዲህ ሶማልያዉያን ጨምሮ በርካታ ሙስሊም ነዋሪዎች በሚገኙባቸዉ ሰባት የዓለም ሃገራት ዜጎች ወደ ዩናይትድ ስቴትስ እንዳይገቡ ማገዳቸዉ ይታወሳል። የፊታችን ማክሰኞ በዩናይትድ ስቴትስ ስ የሚካሄደዉን ፕሬዚዳንታዊ ምርቻ ተከትሎ በኬንያ የሚኖሩ የሶማልያ ስደተኞች እገዳዉ ከትራምፖፕ የምርጫ መሸነፍ ጋር ሊነሳ ይችላል የሚል ተስፋን ሰንቀዋል። በአሜሪካ ለመኖር የጥገኝነት ፈቃድን ካገኙ ሶማልያዉያን ስደተኞች መካከል በናይሮቢ ነዋሪ የሆኑት የአምስት ልጆች እናትዋ ማካ ዳላላ ካባሬ ይገኙበታል። ካባሬ በዩናይትድ ስቴትስ የመኖርያ ፈቃድን አግኝተዉ ወደ ዩናይትድ ስቴትስ ለመጓዝ እቅድ ላይ ሳሉ ነበር ይህ የትራምፕ ሕግ ፀድቆ ከጉዞአቸዉ ያደናቀፋቸዉ። ሶማልያዊትዋ የአምስት ልጆች እናት ገሚሶቹ ልጆቻቸዉ በአሜሪካ የተሰጣቸዉን የመኖርያ ፈቃድ አሟልተዉ አሜሪካ ናቸዉ ግማሹ  ደግሞ ከእናታቸዉ ለመሄድ ዝግጅት ላይ ነበሩ ይላሉ ሶማልያዊትዋ እናት።

«ኑሮአችን ስያት ዉስጥ ለማድረግ ፈቃድ አግኝተል ። እዝያ ለመኖር ሁሉን ነገር አዘጋጅተን ሳለን ነዉ በትራምፕ እገዳ የተጎዳነዉ። እኔ እና ልጆቼ ተለያይተናል። የተወሰኑት ልጆቼ አሜሪካን ገብተዋል። እኔ ግን ተገልያለሁ ፤ ለምን እንደሆን አላዉቅም ምንም የቀረኝ ነገር የለም። የቤተሰቦቼ አስተዳዳሪ ነበርኩ ። በጎርጎረሳዊዉ 2016 ዓ.ም መጀመርያ ላይ ሦስቱ ልጆቼ ወደ አሜሪካ ተወሰዱ። ሁለቱ ልጆቼ እንደድል ሆኖ ከእኔጋ ሳንጓዝ ቀረን እና እዚሁ ቀርተናል።  ይኸዉ ለአራት ዓመታት ናይሮቢ ዉስጥ ተሰናክለን ተቀምጠናል። ምንም የመጣልን ነገር የለም። »

Traumaarbeit Flüchtlinge Kenia
ምስል DW/S. Maingi

በኬንያ የሚኖሩ አብዛኞች አፍሪቃዉያን ስደተኞች ኑሮን ታግለዉ በምዕራብ ሃገራት ጥገኝነት ለማግኘት እና ኑሮአቸዉን ለመመስረት ይጥራሉ። በአሜሪካ ዉስጥ በጥገኝነት ለመኖር ፈቃድ ካገኙት እና የተሟላ ዝግጅትን ካጠናቀቁት የሶማልያ ስደተኞች መካከል አቡበከር ሰዒድ አንዱ ነዉ አቡበከር ትራምፕ ወደ ስልጣን በመምጣታቸዉ እና ሶማልያዉያን ወደ አሜሪካ እንዳይገቡ እገዳ ከተጣለ በኋላ ወደ ሃገሪቱ ተመልሶ የመግባቱ እድል የመነመነ መሆኑን ይናገራል ስለሆነም ይላል በኪንያ በችግር ከማለቃችን በፊት የተባበሩት መንግስታት የስደተኞች ጉዳይ ከፍተና ኮሚሽን «UNHCR» ወደ ሌላ ሀገር በጥገኝነት ያዘዉረን።

«እስካሁን ምንም አይነት መፍትሄን አላገኘንም ። ትራምፕ ወደ አሜሪካ መግባት አይችሉም ካልዋቸዉ ሰዎች መካከል አንዱ ነኝ ። ኬንያዊ አይደለንም የሶማልያ ስደተኞች ነን። እዚህ ያለዉ ሁኔታ በጣም ከባድ እንደሆነ ልታዩ ትችላላችሁ። አሁን ደሞ የኮሮና ተኅዋሲ ስርችት ነገሩን ሁሉ ዉስብስብ አድርጎታል።  ስራ አጦች ነን ምንም የወደፊት ተስፋ የሌለን ስደተኞች መሆናችንን ታያላችሁ ጉዳያችን ትኩረት እንዲያገኝ ወይም ወደ ሌላ ሀገር እንዲዛወር ለተባበሩት መንግሥታት እንጠይቃለን።»

በናይሮቢ የሚኖሩ ሶማልያዉያን ብቻ ሳይሆኑ ዓለም  በሚቀጥለዉ ሳምንት በዩናይትድ ስቴትስ የሚካሄደዉን ፕሬዚዳንታዊ ምርጫና ዉጤቱን እየጠበቀ ነዉ። በእርግጥ የትራምፕ  ሽንፈት የጥገንነት ፈቃድ ያገኙ ሶማልያዉያን ስደተኞች ወደ አሜሪካ የመግባት እድል ያመጣ ይሆን ?

 

አዜብ ታደሰ  

ማንተጋፍቶት ስለሺ