ስደተኞች እና የአውሮጳ የፍልሰት ፖሊሲ
ሐሙስ፣ መስከረም 17 2011ማስታወቂያ
ይሁንና፣ ፈረንሳይ ቆየት ብላ አቋሟን በማለሳለስ በመረከቧ አኳሪየስ ከተሳፈሩት ስደተኞች መካከል 18 ን ተቀብላለች። ቀሪዎቹን ስደተኞች ደግሞ ጀርመን፣ ስጳኝ፣ ማልታ እና ፖርቱጋል ተከፋፍለው ለመቀበል ተስማምተዋል። ይሁንና፣ የፓናማ መንግሥት የዚችኑ በሜድትሬንየን ባህር ስደተኞችን ከሚያጋጥማቸው የመስመጥ አደጋ በማዳኑ ተግባር ላይ የተሰማራችውን አኳርየስ የተባለችውን መርከብ ፈቃድ ሰሞኑን ያነሳበት ድርጊት ኅልውናዋን አደጋ ላይ ጥሎታል። ይህን ተከትሎ ጉዳዩ ያሳሰባቸው ዓለም አቀፉ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅት ፣ አምነስቲ ኢንተርናሽናል እና መሰል ተቋማት የአውሮጳ ህብረት ሀገራት ተደጋግሞ ለሚታየው ቀውስ አፋጣኝ መፍትሔ እንዲፈልጉለት ጠይቀዋል።
ሀይማኖት ጥሩነህ
አርያም ተክሌ
ሸዋዬ ለገሠ