1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ስዕል ላይ ሙሉ ጊዜውን ሰጥቶ የሚንቀሳቀስ ወጣት 

እሑድ፣ ጥር 1 2014

ሰአሊ ታረቀኝ ብዙ ሰአልያን ያደጉበት ማህበረሰብ፣ የትምህርት አይነት፣ ያሳለፉት የፍስሃም ሆነ የመከራ ጊዜ የሚመለከቱትና የሚመስጣችው የተፈጥሮ መልክአ ምድር፣ የሕይወት ፍልስፍና ላይ አተኩረው መሳል ያዘወትራሉ። ሰአሊው በአፍሪካ በተለያዩ ጊዝያት የኖሩ ህዝቦች እንደትእምርት ይጠቀሙባቸው የነበሩ ምልክቶች ላይ ነው ትኩረት አድርጎ የሚስለው

https://p.dw.com/p/45G1G

መዝናኛ፦ ስዕል ላይ ሙሉ ጊዜውን ሰጥቶ የሚንቀሳቀስ ወጣት 

ወደ ስዕል መችና እንዴት እንደገባ በውል አያቀውም። የስዕል ሙያ ትምህርት ቤት ገብቶ ከመመረቁ በፊትም ከህጻንነቱ ጀምሮ ባገኘው አጋጣሚ የመጣለትን ሐሳብ በሰዕል የመግለጽ ዝንባሌውን አዳሯብል። ወጣቱ ሰአሊና የስዕል ሙያ አስተማሪ ታረቀኝ መኮንን። በልጅነቱ በሒሳብም ይሁን በሌላ የትምህርት አይነት ደብተሮች ስዕሎችን ይስል እንደነበረ አጫወቶናል።

 

ብዙ ሰአልያን ያደጉበት ማህበረሰብ፣ የትምህርት አይነት፣ ያሳለፉት የፍስሃም ሆነ የመከራ ጊዜ፣ የሚመለከቱትና የሚመስጣችው የተፈጥሮ መልክአ ምድር፣ የሚከተሉት የሕይወት ፍልስፍና እና ውበት ላይ አተኩረው መሳል ያዘወትራሉ። ሰአሊ ታረቀኝ ደግሞ በኢትዮጵያና በአፍሪካ በተለያዩ ጊዝያት የኖሩ ህዝቦች እንደትእምርት ይጠቀሙባቸው የነበሩ ምልክቶች ላይ ነው ትኩረት አድርጎ የሚስለው።

Äthiopien I Maler und Lehrer
ምስል DW

 

በጥበብ አለም ውስጥ ያሉ ሰዎች ሐሳቦችን አምጠው ለመውለድ ወልደውም እንደየዘርፋቸው የስነ ጽሁፍ፣ የሙዚቃ፣ የስዕል ቅርጽ አስይዘው ተፈላጊውን መልእክት ለመቅረጽ የተለያየ ቦታና ጊዜ ይመርጣሉ። አንዳንዱ ጸጥ ያለ ለዛውም ሳቢና መሳጭ የተፈጥሮ አካባቢን ሲመርጥ ሌላው ጸጥታን ያግኝ እንጂ በቤት ውስጥም ቢሆን ግድ የሌለው አለ።  ሰአሊና መምህር ታረቀኝ ለስእል፣ ሙዚቃና ጽሑፍ የተለያየ ቦታና ሁኔታዎችን እንደሚመርጥ አጫውቶናል።

 

ሰዕል ትምህርት ቤት የተመረቀው ታረቀኝ ከተግባረእድ በአሌክትሮኒክስ፣ ከሙዚቃ ትምህርት ቤት ደግሞ ኪቦርድን ተምሯል። በሙዚቃው አለም ግጥምና ሙዚቃ ደርሶ ለአድማጭ ጀሮ ባያደርስም እስካሁን በዚሁ ዘርፍም ዳድ ዳር እያለ ነው።

 

ታረቀኝ ውስጡን በሙዚቃ ያዳምጣል፣ በሙዚቃ ይደመማል፣ በሙዚቃ ብሶቱን ይገልጻል። በስነ መለኮትም ትምህርቱን እየቀጠለ እንደሆነ ነግሮናል። መንፍሳዊ መዝሙሮችንም እንደሚሞካከር ጭምር።

Äthiopien I Maler und Lehrer
ምስል DW

ሰአሊ ታረቀኝ የጥበብ ተስጦ ኖሮአቸው መድረኩን ላላገኙ ወጥቶች በየሳምንቱ የመገናኛ መድረክ በመፍጠር መክሊታቸውን እንዲፈትሹና ተስጦአቸውን አውቀው መንገዳቸውን ከወዲሁ እንዲያስተካክሉ እንዲረዳቸው በማሰብ በጥበብ ምሽት እንዲታደሙ በመድረግ ላይ እንደሆነ አጫውቶናል።

 

በጥበብ ምሽቱ ከጥበባዊ ጉዳዮች በተጨማሪ በተለያዩ አገራዊ ጉዳዮች  ነጻ ሐሳቦች እንዲንሸራሸሩ ይደረጋል። በዚህ መድረክ የሐሳብ ገደብ የለም፣ ማንኛውም ታዳሚ በመሰለው ርእሰጉዳይ የመሰለውን ሐሳብ በመድረኩ ያለገደብ እንዲገልጽ በማድረግ የሰዎች የመናገር ነጻነነት ልምምድ እንደሚካሔድ ነግሮናል።

በሙዚቃ፣ ስነሁፍና ሰዕል ዘርፎች የተሰማራው ወጣት ታረቀኝ ሙሉ ጊዜውን ሰጥቶ መቀጠል የሚፈልገው በስዕል ዘርፍ እንደሆነ ገልጾልናል።

ዮሐንስ ገብረእግዚአብሔር

ነጋሽ መሃመድ