ስኮሊኦስስ እና ኪፎሲስ
ማክሰኞ፣ ነሐሴ 25 2013ማስታወቂያ
በህክምናው ሳይንስ አጠራር ስኮሊኦስስ እና ኪፎሊሲስ ይባል በጀርባ አጥንት ወይም ህብለ ሰረሰር ላይ የሚከሰት ጉብጠት ነው። የጤና ችግሩ ተመሳሳይ ይመስል እንጂ የሚሰትበት ቦታና መስንኤው የተለያየ መሆኑን የአጥንት ህክምና ከፍተኛ ባለሙያው ዶክተር ውብታየ ዱሬሳ ተክሌ ይናገራሉ። ህብለ ሰረሰር ላይ የሚከሰተው እብጠት ዕድሜ ገፍቶ የሚከሰትበት አጋጣሚ እንዳለ ሁሉ እንዲህ ሆነው የሚወለዱ ሕጻናትም እንዳሉም ነው የአጥንት ህክምና ከፍተኛ ባለሙያው የገለጹልን።
ኪፎሊሲስ እና ስኮሊኦስስ አንድ የሚያደርጋቸው በጀርባ አጥንት ላይ የሚከሰቱ ችግሮች መሆናቸውን የገለጹት አጥንት ከፍተና ህክምና ባለሙያው ብዙውን ጊዜ ኪፎሲስ በሁለት ወይም በሦስት አጥንቶች መካከል የሚፈጠር ሲሆን፤ ችግሩ ያጋጠመው ሰው አንገቱ ስብር ብሎ አጎንብሶ ለመሄድ እንደሚገደድ ነው የተናገሩት። በዚያም ላይ በሁሉም የጀርባ አጥንት አካባቢ ወደላይ ከፍ ብሎ፣ ከመካከል ወይም ዝቅ ብሎም ሊፈጠር ይችላል፤ ስኮሊኦሲስ ግን አጥንቱ ጎብጦ የተጠማዘዘ እንደሚሆን እና በተለይ ደግሞ የሚፈጠረው በሳንባ ማቀፊያ አጥንቶች አካባቢ እንደሆነ ገልጸዋል። ሙያዊ ማብራሪያ የሰጡንን የአጥንት ከፍተኛ ህክምና ባለሙያ ዶክተር ውብታየንም እናመሰግናለን።
ሙሉ ማብራሪያውን ለማድመጥ የድምጽ ማዕቀፉን ይጫኑ።
ሸዋዬ ለገሠ
ኂሩት መለሰ