ስለአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ የነዋሪዎችና የሕግ ባለሙያ አስተያየት
ሐሙስ፣ ጥቅምት 25 2014ማስታወቂያ
መፍትሄ አልባ ሆኖ ተባብሶ የቀጠለውን አንድ ዓመት የደፈነ የሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነትን ተክትሎ ኢትዮጵያ ያወጀችው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ዛሬ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ፀድቆ ወደ ተግባር ገብቷል። ጦርነቱ በተለይም ባለፈው ሳምንት መጨረሻ ወደ አጎራባች አከባቢዎች መስፋፋቱን ተከትሎ በተለያዩ አከባቢም የአለመረጋጋትን ስጋት በማጫሩ የአዋጁን አስፈላጊነት የሚጋሩ ዜጎችም በርካቶች ናቸው። አስተያየታቸውን ለዶይቼ ቬለ የሰጡት የሕግ ተንታኝ እንዳሉትም በመደበኛ ጊዜ የሚጠበቁትን ሰብዓዊ መብቶች ሊደፈጥጥ የሚችለውን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ማወጅ ባይወደድም ለአሁናዊ የኢትዮጵያ ሁኔታ አስፈላጊ ነው ይላሉ።
ስዩም ጌቱ
ሸዋዬ ለገሠ
ማንተጋፍቶት ስለሺ