ስለተራዘመው የሕዝብ ቆጠራ የአብን መግለጫ
ማክሰኞ፣ መጋቢት 10 2011ማስታወቂያ
የአማራ ብሄራዊ ንቅናቄ (አብን) 4ኛው የህዝብና ቤቶች ቆጠራ መራዘሙ ተገቢ ቢሆንም፤ በ3ኛው ህዝብና ቤቶች ቆጠራ የተሳተፉ አመራሮች እንዲጠየቁ፣ መንግስት ይቅርታ እንዲጠይቅ፣ ውጤቱም በይፋ እንዲሰረዝ እና ካሳ ለሚገባቸው እንዲከፈል ጠየቀ። ፓርቲው በ3ኛው የህዝብ እና ቤቶች ቆጠራ ወቅት በአማራ ፣ በአዲስ አበባ ፣ በጉራጌ እና በቅማንት ህዝቦች ላይ ፖለቲካዊ የሆነ ህዝብን ያለመቁጥር የተቆጠረውንም ያለማሳወቅ ወንጀል ተሰርቷል ብሏል። በመሆኑም የህግ ማዕቀፉና መዋቅሩ ተስተካክሎ ግልጽነትና ተጠያቂነት ያለበት አሰራር መስፈኑ ሲረጋገጥና አገሪቱ ያለችበት ወቅታዊ የመፈናቀል ችግር ሲቀረፍ ብቻ አሁን የተራዘመው የህዝብና ቤቶች ቆጠራ ሊከናወን ይገባል ሲል ዛሬ በሰጠው መግለጫ አመልክቷል። ለዝርዝሩ ሰለሞን ሙጬ ከአዲስ አበባ።
ሰለሞን ሙጬ
ማንተጋፍቶት ስለሺ
አዜብ ታደሰ