1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ስለ አፋር ጥቃት ቃለመጠይቅ

ረቡዕ፣ ጥቅምት 3 2014

ሐራ ከሚባለው ሥፍራ የሕወሓት ታጣቂዎች ወደ አፋር ክልል እዋ ወረዳ አደረሱ በተባለው ተደጋጋሚ የመድፍ ጥቃት ሰላማዊ ሰዎች በአሰቃቂ ሁኔታ መገደላቸውን የአፋር ሰብአዊ መብቶች ድርጅት ዐስታወቀ። ከከፍታማ ቦታዎች ላይ የሚተኮሱ መድፎች ወደ አፋር ክልል 20 እና 30 ኪሎ ሜትሮች ርቀት ከተማ ደብድበዋል ተብሏል።

https://p.dw.com/p/41ctC
Äthiopien Spezialeinheiten der Armee und Milizen in der Region Afar
ምስል Seyoum Getu/DW

ሰላማዊ ሰዎች ዒላማ መሆናቸው ተገልጧል

ሐራ ከሚባለው ሥፍራ የሕወሓት ታጣቂዎች ወደ አፋር ክልል እዋ ወረዳ  አደረሱ በተባለው ተደጋጋሚ የመድፍ ጥቃት ሰላማዊ ሰዎች በአሰቃቂ ሁኔታ መገደላቸውን የአፋር ሰብአዊ መብቶች ድርጅት ዐስታወቀ። ከከፍታማ ቦታዎች ላይ የሚተኮሱ መድፎች ወደ አፋር ክልል 20 እና 30 ኪሎ ሜትሮች ርቀት ከተማ ደብድበዋል ተብሏል። የሕወሓት ኃይሎች በመድፍ ጥቃቶቹ ሰላማዊ ሰዎችንም ገድለዋል ሲሉ የአፋር ሰብአዊ መብቶች ድርጅት አቶ ገአስ አህመድ ለዶይቸ ቬለ ተናግረዋል። 

የሕወሓት ቃል አቀባይ አቶ ጌታቸው ረዳ፦ ሰላማዊ ሰዎች ላይ ጥቃት አላደረስንም ሲሉ ለፈረንሳይ የዜና ወኪል (AFP)ተናግረዋል። አቶ ገአስ ጥቃቱ ሰላማዊ ሰዎች ላይ የደረሰው የአፋር ኃይሎች ከዚህ ቀደም ሕወሓትን ከክልሉ በማባረራቸው በበቀል ድርጊት ነው ብለዋል። ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ስለ አፋር ሰላማዊ ሰዎች ግድያ እና ጥቃት «ጆሮ ዳባ ማለቱን ያብቃ» ብለዋል። አቶ ገአስን ስቱዲዮ ከመግባቴ በፊት በስልክ አነጋግሬያቸው ነበር። ጥቃቱ ምን ይመስል እንደነበር፤ ስላደረሰውም ጉዳት በማብራራት ይጀምራሉ። 

ማንተጋፍቶት ስለሺ
ኂሩት መለሰ