1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ስለ ሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት አስተያየት

ሐሙስ፣ መስከረም 12 2015

በሰሜን ኢትዮጵያ በአዲስ መልክ ያገረሸው ጦርነት ዘላቂ እልባት የሚያገኘው ተፋላሚ ኃይላቱ ከልባቸው ለሰላም መዘጋጀታቸውን ሲያረጋግጡ ብቻ ነው ተባለ፡፡ አስተያየታቸውን ለዶይቼ ቬለ የሰጡ የአዲስ አበባ ነዋሪዎች እንዳመለከቱት የበርካታ ዜጎችን ሕይወት የቀጠፈውና የአገር ኢኮኖሚን ያወደመው ጦርነት የማያዳግም እልባት ያሻዋል፡፡

https://p.dw.com/p/4HEH8
Äthiopien Addis Abeba Stadtansicht
ምስል Solomon Muchie/DW

አስተያየት ሰጪዎች ጦርነቱ እልባት ያሻዋል ብለዋል

በሰሜን ኢትዮጵያ በአዲስ መልክ ያገረሸው ጦርነት ዘላቂ እልባት የሚያገኘው ተፋላሚ ኃይላቱ ከልባቸው ለሰላም መዘጋጀታቸውን ሲያረጋግጡ ብቻ ነው ተባለ፡፡ አስተያየታቸውን ለዶይቼ ቬለ የሰጡ የአዲስ አበባ ነዋሪዎች እንዳመለከቱት የበርካታ ዜጎችን ሕይወት የቀጠፈውና የአገር ኢኮኖሚን ያወደመው ጦርነት የማያዳግም እልባት ያሻዋል፡፡

በአፍሪካ ቀንድ የአሜሪካ ልዩ መልእክተኛ ማይክ ሐመር ከትናንት በስቲያ በኢትዮጵያ ጦርነቱ የሚቆምበት አግባብ ላይ መፍትሄ የማፈላለግ በኢትዮጵያ የ10 ቀናት የዲፕሎማሲያዊ ቆይታቸውን በማስመልከት በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ፤ “በሰሜን ኢትዮጵያው ጦርነት የኤርትራ ሰራዊት ተሳትፎ ያሳስበናል እንቃወማለንም” ብለው ነበር፡፡
ዶይቼ ቬለ በዚሁ ላይ አስተያየታቸውን የጠየቃቸው የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪዎች እንዳሉትም መሰል የጦርነት ስልት መፍትሄ ከማምጣት ይልቅ በትውልድ መሃል ቁርሾን ጥሎ የማለፍ እድሉ ሰፊ መሆኑን ነው ያብራሩት፡፡

በሰሜኑ የኢትዮጵያ ክፍል ሌላኛው አስከፊ የጦርነቱ ገጽታ ውስጥ ስለመግባታቸው የሚነገረው የኢትዮጵያ መንግስት እና ለአንድ ዓመት ገደማ ያለፌዴራሉ መንግስት ዕውቅና ትግራይ ክልልን እያስተዳደረ ያለው ህዝባዊ ወያኔ ኃርነት ትግራይ (ህወሓት) ለአምስት ወራት ያህል ባደረጉት የተናጥል ተኩስ አቁም ስምምነት ወደ ሰላማዊ ድርድር የመሄድ ተስፋን አሰንቀው ነበር፡፡

እንደ አዲስ አበባ ነዋሪዎች አስተያትም በአፍሪካ ህብረት መርህ ስር ሊካሄድ ጥረቱ እየተገፋ ባለው የሰላም አማራጭ ሁሉም ተፋላሚ ሃይላት ተሰባስበው ከልባቸው ቢመክሩ ልደርስ የሚችለውን ውድመት የመቀነስ እድል ይኖራል፡፡ በእርግጥ ለዚህ ጦርነት መቋጫው ኃይልን እንደ አማራጭ መውሰድ ብቻ ነው ያሉም አልጠፉም፡፡ እነዚህ አስተያየት ሰጪዎች የተፋላሚ ኃይላት በተለይም የህወሓት ተደራዳሪዎች የሰላም ጥሪ ከልብ ያልሆነ በሚል ይወቅሳሉ፡፡

 Addis Ababa City
ምስል Seyoum Getu/DW

በሰሜን ኢትዮጵያ እየተካሄደ ያለው ጦርነት ዳፋው በአከባቢው ብቻ የማይወሰን መሆኑን ግን ሁሉም ይስማሙበታል፡፡ በኢዮጵያ በተለያዩ አከባቢዎች ለሚስተዋሉ አለመረጋጋቶችና የዜጎች ሰቆቃ ይህ የሰሜን ኢትዮጵያው የጎላ ውጊያ የማያሟግት ድርሻ አለው ሲሉም ይገልጹታል፡፡ ጦርነቱ በአፋጣኝ ተቋጭቶ ዘላቂ መፍትሄ ካላገኘም የዜጎች እልቂት እና የኢኮኖሚ ድቀቱ የማይቀር እዳ ነው ሲሉም አስተያየት ሰጪዎቹ ሃሳባቸውን አክለው አብራርተዋል፡፡ በሰሜን ኢትዮጵያ የሚካሄደውን ጦርነት በሰላማዊ መንገድ የመቋጨት አማራጭ ገቢራዊ እንዲሆን ዓለማቀፉ ማህበረሰብም እየወተወቱ ነው፡፡ 

ሰሞኑን በኢትዮጵያ የ10 ቀናት ቆይታ አድርገው ወደ አገራቸው አሜሪካ የተመለሱት በምስራቅ አፍሪካ የዩናይትድ ስቴትስ የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መእልክተኛ ማይክ ሐመር “ተፋላሚዎችን ወደ አንድ ለማምጣት ዋናውና መሰረታዊው ጉዳይ መተማመንን በሂደት መገንባት ነው፡፡” ብለው ነበር፡፡ በጦርነቱ የተሰቃዩት ህዝብ መካከልም ይህን የመተማመን ስሜት ማስረጽ ያስፈልጋል፡፡ ሲሉ አስተያየታቸውን ያከሉት ሐመር ልዑካቸው ከሌሎች ዓለማቀፍ ማህበረሰብ ጋር በመሆን ይንኑን መተማመን የሚያመጣ ሂደቶችት ለማስከተል ተስፋዎችን ማየታቸውንም አንስተው ነበር፡፡ 

በሰሜን ኢትዮጵያ ትግራይ ክልል ውስጥ በኢትዮጵያ እና ኤርትራ ኃይሎች መንግስትነን በሚወጋው የህወሓት ኃይሎች ላይ ሰፊ ጥቃት እንደከፈቱባቸው እየተገለጸ ነው፡፡ የክልሉ ከፍተኛ ባለሥልጣን አቶ ጌታቸው ረዳ በሰጡት መግለጫ የኢትዮጵያ እና ኤርትራ መንግሥት ኃይሎች ከመስከረም 10 ቀን 2015 ዓ.ም. ጀምረው በተለያዩ ግንባሮች ትግራይ ላይ ሰፊ ጥቃት ከፍተዋል ብለዋል። 

በኢትዮጵያ መንግስት በኩል በአፍሪካ ህብረት መርህ በሚካሄደው የሰላም ድርድር የማያሻማ ጽኑ አቋም መኖሩ ባለፈው ሳምንት በኢትዮጵያ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን በኩል ቢገለጽም ስለ አሁናዊው የሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት በውል የተብራራ ነገር የለም፡፡
ሥዩም ጌቱ

ነጋሽ መሐመድ

ሸዋዬ ለገሰ