1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ስለ ምርጫ ቦርድ የጊዜ ሠሌዳ የትግራይ ፖለቲካ ፓርቲዎች

ረቡዕ፣ ጥር 6 2012

ዛሬ ይፋ በተደረገው የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምርጫ ማስፈፀሚያ ጊዜያዊ መርሐ ግብር ላይ የተለያዩ የፖለቲካ ፓርቲዎች አስተያየት እየሰጡ ነው፡፡ ሀገራዊው ምርጫ እንዲካሄድ በተደጋጋሚ ሲጠይቅ የቆየው ህዝባዊ ወያኔ ሀርነት ትግራይ( ህወሓት) ምርጫውን ለማካሄድ የሚደረጉ እንቅስቃሴዎችን በአዎንታዊነት እንደሚመለከተው ገልጿል፡፡

https://p.dw.com/p/3WFhQ
Nationales Wahlgremium Äthiopiens
ምስል DW/S. Muchie

ሀገራዊ ምርጫ ማስፈፀሚያ ጊዜያዊ መርሐ ግብር ይፋ ኾነ

ዛሬ ይፋ በተደረገው የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምርጫ ማስፈፀሚያ ጊዜያዊ መርሐ ግብር ላይ የተለያዩ የፖለቲካ ፓርቲዎች አስተያየት እየሰጡ ነው፡፡ ሀገራዊው ምርጫ እንዲካሄድ በተደጋጋሚ ሲጠይቅ የቆየው ህዝባዊ ወያኔ ሀርነት ትግራይ( ህወሓት) ምርጫውን ለማካሄድ የሚደረጉ እንቅስቃሴዎችን በአዎንታዊነት እንደሚመለከተው ገልጿል፡፡ በሌላ በኩል በክልሉ የሚንቀሳቀሰው ተቃዋሚው ሳልሳይ ወያነ ትግራይ ምርጫውን በክረምት ወቅት ለማድረግ መርሐግብር መውጣቱ የአብዛኛውን ህዝብ ሁኔታ ያላገናዘበ ብሎታል፡፡ ለረጅም ዓመታት በትግራይ ክልል በተቃዋሚነት እየተንቀሳቀሰ የዘለቀው ዓረና ትግራይ በበኩሉ ከምርጫ ማስፈፀሚያ ጊዜያዊ መርሐግብሩ ይልቅ በክልሉ ያለው የፖለቲካ ምህዳር መጥበብ እንደሚያሳስበው በሊቀ መንበሩ በኩል ገልጿል፡፡  
ሚሊዮን ኃይለሥላሴ
ማንተጋፍቶት ስለሺ
ኂሩት መለሰ