1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ስለ ሊቢያ ጸጥታ የአውሮጳ ኅብረት መከረ

ማክሰኞ፣ ጥር 12 2012

የአውሮጳ ኅብረት የውጭ ጉዳይ ሚንሥትሮች ትናንት ቤልጂየም ብራስልስ ውስጥ ተሰብስበው የወቅቱ የዓለም በተለይም ደግሞ የአውሮጳ ዋና አጀንዳዎች ባሏቸው የሊቢያ የጸጥታ ኹኔታ እና የኢራን የኒውክሌር ስምምነት ላይ መክረዋል።

https://p.dw.com/p/3WaNy
Belgien Europäische Kommission in Brüssel
ምስል picture-alliance/dpa/D. Kalker

በአውሮጳ ኅብረት የሊቢያ ጉዳይ ዋነኛ መነጋገሪያ ኾኗል

የአውሮጳ ኅብረት የውጭ ጉዳይ ሚንሥትሮች ትናንት ቤልጂየም ብራስልስ ውስጥ ተሰብስበው የወቅቱ የዓለም በተለይም ደግሞ የአውሮጳ ዋና አጀንዳዎች ባሏቸው የሊቢያ የጸጥታ ኹኔታ እና የኢራን የኒውክሌር ስምምነት ላይ መክረዋል። በሳምንቱ መጨረሻ ላይ ጀርመን በሊቢያ ቀውስ ላይ ለመምከር ባዘጋጀችው የበርሊኑ ጉባኤ የዓለም መሪዎች መሳተፋቸው ይታወሳል። የሊቢያ ቀውስ ከሊቢያም ባሻገር ጎረቤት ሃገራት እና ባሕር ተሻግሮ አውሮጳ መድረሱም አሳስቧል። ከሊቢያ በስተደቡብ የሚገኙት የሣኅል አካባቢ ሃገራት በመባል የሚታወቁት ሞሪታንያ፣  ቡርኪናፋሶ፤ ቻድ፤ ማሊ እና ኒጀር በተለይ በሊቢያ መፍረስ ምክንያት ሰላማቸው ታውኳል፤ አሸባሪዎችም በሃገራቱ እንደተስፋፉባቸው ነው የሚታወቀው። ባለፉት ጥቂት ዓመታት ብቻ በእነዚህ የሣኅል አካባቢ ሃገራት ከ150 በላይ ወታደሮች እና ከ4000 በላይ ሰላማዊ ሰዎች መገደላቸው ተገልጧል።  

ገበያው ንጉሤ 

ማንተጋፍቶት ስለሺ

ነጋሽ መሐመድ