ሴቶችን ወደውሳኔ ሰጭነት የማሳደግ ዕድል እና ተግዳሮት
ሰኞ፣ ነሐሴ 13 2011ማስታወቂያ
የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ሴቶችን ወደ ውሳኔ ሰጭነት ለማምጣት በሚያጋጥሙ ተግዳሮቶች እና ዕደሎች ላይ የሚመክር የፓናል ውይይት ዛሬ በሀዋሳ ከተማ አካሂዷል። በፓናል ውይይቱ ላይ ሴቶች እራሳቸውን ለማብቃት በሚያደርጉት ጥረት ከሚያጋጥሞቸው ችግሮች መካከል የፆታ ትንኮሳ እና ጥቃት በዋነኝነት እንደሚጠቀስ ተገልጿል ። የሴቶችን መብት የሚመለከቱ ጉዳዮችን ከመረዳት አኳያ በአካዳሚው የትምህረት ሂደት የትኛውም ደረጃ ላይ መገኘት በቂ ግንዛቤ ለመኖሩ ማሳያ እንደማይሆንም ተጠቅሷል። የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ዛሬ በሀዋሳ ከተማ ባዘጋጀው የፓናል ውይይት / ሴቶችን ወደ ውሳኔ ሰጭነት ለማምጣት በሚያጋጥሙ ተግዳሮቶች እና ዕድሎች ላይ የተለያዩ ሃሳቦች ተነስተው ውይይት ተደርጎባቸዋል ። ውይይቱን የተከታተለው የሀዋሳው ወኪላችን ሸዋንግዛው ወጋየሁ ተከታዩን ዘገባ ልኮልናል።
ሸዋንግዛው ወጋየሁ
ሸዋዬ ለገሠ
አዜብ ታደሰ