ሲዳማ ክልል፣ 12 ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት መሰረቱ
ሐሙስ፣ መጋቢት 2 2013ማስታወቂያ
በመጪው አገራዊ ምርጫ ለመወዳደር በሲዳማ የምርጫ ክልሎች የሚንቀሳቀሱ 12 ፓርቲዎች «በምርጫ ሂደት ሊነሱ የሚችሉ ቅሬታዎችና አለመግባባቶችን በውይይት ለመፍታት ያስችለናል» ያሉትን የጋራ ምክር ቤት መሰረቱ። ፓርቲዎቹ የአገሪቱን ሕግ ለማክበርና ሰላማዊ የምርጫ ፉክክር ለማድረግ አጋዥ የሆኑ የስነ ምግባር ደንቦችና የቃል ኪዳን ሰነዶችንም ተፈራርመዋል። የጋራ ምክር ቤቱን መቋቋም ያወደሱት የኢትዮጲያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ የስራ ሃላፊዎች በበኩላቸው የምክር ቤቱ መመስረት አንድም ተፎካካሪ ፓርቲዎችን ያቀራርባል፣ ሁለትም በምርጫ አፈጻጸም የሚጋጥሙ ችግሮችን በምክክር ለመፍታት ያስችላል ብለዋል።
ሸዋንግዛዉ ወጋየሁ
ማንተጋፍቶት ስለሺ
አዜብ ታደሰ