1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ሲቪክ ድርጅቶች ለአሜሪካ መንግሥት ያቀረቡት ጥያቄ

ረቡዕ፣ ነሐሴ 26 2013

ወልቃይትንና አካባቢውን አስመልክቶ ያዘውን አቋም በመቃወም 13 ሲቪክ ድርጅቶች ለዩናይትድ ስቴትስ መንግሥት ደብዳቤ አስገቡ።

https://p.dw.com/p/3zmw2
Weltspiegel 09.02.2021 | USA Impeachment | Washington Capitol Hill
ምስል Sarah Silbiger/Getty Images

13 ሲቪክ ድርጅቶች ለአሜሪካ መንግሥት ደብዳቤ ማስገባታቸው

ወልቃይትንና አካባቢውን አስመልክቶ ያዘውን አቋም በመቃወም ለዩናይትድ ስቴትስ መንግሥት ደብዳቤ ማስገባታቸውን 13 ሲቪክ ድርጅቶች አስታወቁ። የድርጅቶቹ ተወካዮች ዶክተር ሠናይት ደረጀ እና አቶ ዐቢይ በለው አካባቢዎቹ የአማራ ሆነው ሳለ በአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከንና ቃል አቀባያቸው በኩል ምዕራብ ትግራይ ተብለው በተደጋጋሚ መጠቀሳቸው የተሳሳተና አግባብነት የሌለው መሆኑን ለዶይቸ ቬለ ገልጸዋል። ስለጉዳዩ ዶቼ ቬለ የጠየቃቸው በሲያትል የሚኖሩት ጋዜጠኛ አብርሃ በላይ በበኩላቸው ወልቃይትና አካባቢው አሁን በአማራ ኃይሎች በኃይል የተያዙ የትግራይ ክልል ወሰኖች እንደሆኑ ይናገራሉ።  

ታሪኩ ኃይሉ 

ሸዋዬ ለገሠ

ኂሩት መለሰ