1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ሰነዶች የማረጋገጫ ኤጀንሲ አዲስ አሰራር

ዓርብ፣ ታኅሣሥ 19 2011

የፌዴራል የሰነዶች ማረጋገጫ ኤጀንሲ ሰነዶችን አረጋግጦ በመስጠት ሂደት ውስጥ ይታይ የነበረውን ተገልጋዮችን የሚያንገላታ ፡ ወጭ የሚያስወጣና የተንዛዛ አሰራር መለወጥ የሚያስችል አዲስ ሥርዓት መጀመሩን ይፋ አደረገ። አዲሱ ስልት ሁሉንም የውክልና ፡ የንብረት ዝውውር የስጦታ እንዲሁም መሰል አገልግሎቶችን በኦንላይን የኢንተርኔት የሚያልቅ ነው።

https://p.dw.com/p/3AjqW
Symbolbild Afrika Computer
ምስል Imago/R. Holz

«በአዲሱ ስልት በቀን በሺህ የሚቆጠሩ ሰዎች ማስተናገድ ይቻላል»

 አገልግሎቱን በቀላሉ በእጅ ስልክ አሊያም በኮምፒውተር ማከናወን የሚችል ሲሆን ይህም ጊዜን ፡ ገንዘብን እና አላስፈላጊ እንግልትን ያስቀራል ተብሏል። ኤጀንሲው ይህንን አገልግሎቱን ለሁሉም ለማዳረስም የቅርንጫፍ ጽ/ቤቶቹን ከ 4 ወደ 15 ማሳደግ መቻሉም ተገልጿል። ይህም ሆኖ ግን የኮምፒውተር እና የኢንተርኔት አገልግሎት ማግኘትም በአንዳንድ የግል ኮምፕውተር እና ኢንተርኔት አስጠቃሚ የግል ድርጅቶች አላስፈላጊ የዋጋ ጭማሪ እንዲያደርጉ በር መክፈቱን ለመታዘብ ሞክረናል፡፡ በሌላ በኩል ይህ አገልግሎት በመላው ኢትዮጵ የሚኖሩትን እንጅ በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያንን እንደማያካትት ነው የተገለፀው።  በዛሬው ዕለት የሕግና ፍትህ የመረጃ ሥርአትን በአንድ የመረጃ ቋት ይዞ የመጣና ከ 1934 እስከ 2010 የተጠቃለሉ ሕጎችን በ ኦንላይን ስርአት ማግኘት የሚያስችል መተግበሪያ ሶፍትዌር በፌዴራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ ተዘጋጅቶ ዛሬ ተመርቋል፡፡ ከአዲስ አበባ ሰሎሞን ሙጬ ዝርዝር ዘገባ ልኮልናል።

ሰሎሞን ሙጬ

ሸዋዬ ለገሠ

ነጋሽ መሐመድ