1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ሰብዓዊ ቀውስ በትግራይ 

ዓርብ፣ መጋቢት 16 2014

ቢያንስ ላለፉት አምስት ወራት ምንም ዓይነት እርዳታ እንዳላገኙ የሚገልፁት ከተለያየ የትግራይ አካባቢዎች ተፈናቅለው መቐለ የሚገኙ ዜጎች ይኖሩበት ከነበረ መጠልያ ለቀው ጎዳና መውጣታቸውን ተናግረዋል። በአሁኑ ጊዜ 90 በመቶ የሚሆን ህዝብ፣ እርዳታ ፈላጊ መሆኑን የተለያዩ ዓለምአቀፍ ድርጅቶች ገልጸዋል ሲል ሚሊዮን ኃይለ ስላሴ ከመቀሌ ዘግቧል። 

https://p.dw.com/p/49328
BG Tigray | Mahlet
ምስል Maria Gerth-Niculescu/DW

ሰብዓዊ ቀውስ በትግራይ 


በጦርነቱ ምክንያት ተፈናቅለው በተለያዩ የትግራይ አካባቢዎች የሚገኙ ዜጎች ሰብአዊ እርዳታ ባለማግኘታቸው ለረሀብ መጋለጣቸው ተነገረ። ቢያንስ ላለፉት አምስት ወራት ምንም ዓይነት እርዳታ እንዳላገኙ የሚገልፁት ከተለያየ የትግራይ አካባቢዎች ተፈናቅለው መቐለ የሚገኙ ዜጎች ይኖሩበት ከነበረ መጠልያ ለቀው ጎዳና መውጣታቸውን ተናግረዋል። ትግራይ በአጠቃላይ በከበባ እና የአገልግሎት እገዳ ላይ ባለችበት፣ የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ በተስተጓጎለበት፣ ዜጎች ያስቀመጡትን ገንዘብ ጭምር ከባንክ ማውጣት በማይችሉበት በአሁኑ ወቅት 90 በመቶ የሚሆን  ህዝብ፣ እርዳታ ፈላጊ መሆኑን የተለያዩ ዓለምአቀፍ ድርጅቶች ገልጸዋል ሲል ሚሊዮን ኃይለ ስላሴ ከመቀሌ ዘግቧል። 
ሚሊዮን  ኃይለ ሥላሴ
ኂሩት መለሰ
አዜብ ታደሰ