1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ሰባት ተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች ሊዋሃዱ ነው

ሐሙስ፣ ኅዳር 20 2011

ሰባት የኢትዮጵያ ተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ ለመዋሃድ ተስማሙ። ከሰባቱ አምስቱ ከሀገር ውጭ ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ናቸው።

https://p.dw.com/p/39AQv
Äthiopien | Teshale Sebero auf der Presskonferen der äthiopischen Oppositionspartei
ምስል G. Tedla HG

ሰባት ተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች ሊዋሃዱ ነው

ሰባት የኢትዮጵያ ፖለቲካ ፓርቲዎች በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ ለመዋሃድ ተስማሙ። ከሰባቱ አምስቱ ከሀገር ውጭ ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ናቸው። በሀገር ውስጥ ሲሰሩ የቆዩቱ ሁለት ፓርቲዎች የኢትዮጵያ ራዕይ ፓርቲ እና የኦሞ ህዝቦች ዲሞክራሲያዊ ህብረት ሲሆኑ የኢትዮጵያ ፌደራላዊ የሽግግር ምክር ቤት፣ የኢትዮጵያ መድህን ዲሞክራሲያዊ ፓርቲ፣ ብሩህ ኢትዮጵያ ዲሞክራሲያዊ ንቅናቄ እና ኢትዮጵያችን ህዝባዊ ንቅናቄ ደግሞ መቀመጫቸውን ከሀገር ውጭ ያደረጉ ናቸው።

ሰባቱ ፓርቲዎቹ የአቋም መግባባት ላይ ለመድረስ ለበርካታ ወራት ሲደራደሩ መቆየታቸውን ለDW ተናግረዋል። የአዲስ አበባው ወኪላችን ዩሃንስ ገብረእግዚያብሔር ያጠናቀረውን ሙሉ ዘገባ ለማድመጥ የድምጽ ማዕቀፉን ይጫኑ። 

ዩሃንስ ገብረእግዚያብሔር

ተስፋለም ወልደየስ 

ኂሩት መለሰ