1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ሰሜን ኮርያ ለመጀመርያ ጊዜ በኮሮና ሰዉ መሞቱን ገለፀች

ዓርብ፣ ግንቦት 5 2014

ሰሜን ኮርያ ለመጀመርያ ጊዜ በኮሮና ሰዉ መሞቱን ገለፀች። ይህ የሀገሪቱ መግለጫ የተሰማዉ ሰሜን ኮሪያ በዓለማችን የኮረና ወረርሽኝ ከጀመረበት ጊዜ አንስቶ ለመጀመሪያ ጊዜ በሀገሪቱ የኮቪድ ወረርሽኝ መሰራጨቱን በይፋ ካሳወቀች ከአንድ ቀን በኋላ መሆኑ ነዉ። ሀገሪቱ የቫይረሱን ስርጭት ለመከላከል በመላ ሰሜን ኮርያ ይዝዉዉር እገዳ ተጥሎአል።

https://p.dw.com/p/4BHY2
Nordkorea COVID-19 | Kim Jong Un
ምስል KRT/AP Photo/picture alliance

ሰሜን ኮርያ ለመጀመርያ ጊዜ በኮሮና ሰዉ መሞቱን ገለፀች። ባለስልጣናት በሀገሪቱ በኮሮና ተሐዋሲ የተያዙ ሰዎች መኖራቸዉን ከተናገሩ በኋላ ስድስት ሰዎች «በትኩሳት» ህመም መሞታቸውን የመንግሥት መገናኛ ብዙኃን ዛሬ ዘግቦአል። ትናንት በሰሜን ኮርያ ከ180,000 በላይ ሰዎች በኮሮና ተሐዋሲ መያዛቸዉ እና ዛሬ ደግሞ የኮሮና ተሐዋሲ ምልክት የታየባቸዉ ሰዎች 18,000 በተገለለ ስፍራ ህክምና እየተከታተሉ መሆኑ ነዉ የተነገረዉ። የሰሜን ኮርያዉ መሪ ኪም ዮን ኡን ዛሬ በኮሮና ተሐዋሲ የተያዙ እና አስቸኳይ ህክምና እየተከታተሉ የሚገኙ ሰዎችን ስፍራዉ ድረስ ሄደዉ መጎብኘታቸዉም ተገልፆአል። የሰሜን ኮርያ መንግሥት መገናና አውታር ዛሬ እንደዘገበዉ አፋጣኝ የሕዝብ ጤና ቀውስ ሁኔታን ቀደም ብሎ ለመቀልበስ ፓርቲያችን ፊት ለፊት የሚጋፈጠው በጣም አስፈላጊ እና በዋና ተግባራት ነው ሲል ዘግቧል።  ይህ የሀገሪቱ መግለጫ የተሰማዉ ሰሜን ኮሪያ በዓለማችን የኮረና ወረርሽኝ ከጀመረበት ጊዜ አንስቶ ለመጀመሪያ ጊዜ በሀገሪቱ የኮቪድ ወረርሽኝ መሰራጨቱን በይፋ ካሳወቀች ከአንድ ቀን በኋላ መሆኑ ነዉ። ሀገሪቱ የቫይረሱን ስርጭት ለመከላከል በመላ ሰሜን ኮርያ ይዝዉዉር እገዳ ተጥሎአል።   

 

አዜብ ታደሰ

ማንተጋፍቶት ስለሺ