1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ሰላማዊ የፖለቲካ ትግልና ትጥቅ በኢትዮጵያ

እሑድ፣ ጥቅምት 11 2011

ካለፉት ጥቂት ወራት ወዲህ ከኢትዮጵያ የተለያዩ አካባቢዎች የዜጎች ጥቃት እና መፈናቀልን የሚመለከቱ አቤቱታዎች ጎልተው እየተሰሙ ነው። የጥቃቱ ሰለባዎች፤ ድርጊቱ የሚፈፀመው በታጣቂ ኃይሎች መሆኑንም ይናገራሉ። ትጥቅ ያነገቡት ማንነት ማረጋገጫው ባይገኝም ከዚህ ጋር ተያይዞ ስማቸው የሚነሳ ቡድኖች ግን አሉ።

https://p.dw.com/p/36rC6
Waffen Symbolbild Flash-Galerie
ምስል AP

የትጥቅ ፍቱ አንፈታም አካሄድ ወዴት ያመራል?

መንግሥት ባለፈው ሳምንት በይፋ ነፍጥ አንግቦ በተቃዉሞ ይንቀሳቀስ የነበረው እና በቅርቡ ወደሰላማዊ ትግል መግባቱ የተነገረለት የኦሮሞ ነፃ አውጭ ግንባር በምህጻሩ ኦነግ፤ አባላቱን ትጥቅ እንዲያስፈታ ፤ ያን ካላደረገ ደግሞ መንግሥት ራሱ ይህን ተግባራዊ እንደሚያደርግ አሳስቧል። የኦነግ መሪዎች ለዚህ የሰጡት ምላሽ ማነጋገር ይዟል። በሌላ በኩል ኢትዮጵያ በምትገኝበት የዚህ የሽግግር ወቅት የታጠቁ ቡድኖች ያደርሳሉ ከሚባለው ችግር ባልተናነሰ በኅብረተሰቡ ውስጥም የሚገኘው የጦር መሣሪያ ጥንቃቄ ሊደረግበት እንደሚገባ ምሁራን ይመክራሉ። የዶይቼ ቬለ የዚህ ሳምንት እንወያይ መሰናዶ የትጥቅ ፍቱ አንፈታም አካሄድ ወዴት ያመራል? በዛሬዋ ኢትዮጵያ በሰላማዊ መንገድ የፖለቲካ ሃሳብን ማራመድ እና የጠመንጃ እና ኃይል ፖለቲካስ እንዴት ይታያል? በሚሉት ላይ ምሁራንን አወያይቷል። 

 ሸዋዬ ለገሠ 

ማንትጋፍቶት ስለሺ