1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ሰላማዊ ሰልፍ በድሬዳዋ

ማክሰኞ፣ መስከረም 27 2012

በደቻቱ አከባቢ የሚኖሩ ሴቶች ያካሄዱት ዓይነት ሰላማዊ ሰልፍ  በዛሬው ዕለት ወንዶችም ሴቶችም በተገኙበት በአምስተኛ እና ገንደ ጋራ ተካሂዷል። በዛሬው ዕለት በአስተዳደሩ ህንፃ ፊት ለፊት የኅብረተሰቡ አካላት «ችግር ፈጣሪዎች ተጠያቂ ይሁኑ፣ አስተዳደሩ በየጊዜው ለሚፈጠረው ግጭት ዘላቂ መፍትሄ ይስጥ» የሚሉ እና ሌሎች ጥያቄዎችም አቅርበዋል

https://p.dw.com/p/3QuZn
Äthiopien Stadansicht Dire Dawa
ምስል DW/M. Teklu

ሰላማዊ ሰልፍ በድሬዳዋ

በድሬደዋ ደቻቱ፣ አምስተኛ እና ገንደ ጋራ በተባሉ አካባቢዎች ለተከሰተው ግጭት  መንግስት መፍትሄ ይስጠን ሲሉ የአካባቢው ነዋሪዎች ትናንት እና ዛሬ ባካሄዱት ሰላማዊ ሰልፍ ጠየቁ። በትናንትናው ዕለት በደቻቱ አከባቢ የሚኖሩ ሴቶች ያካሄዱት ዓይነት ሰላማዊ ሰልፍ  በዛሬው ዕለት ወንዶችም ሴቶችም በተገኙበት በአምስተኛ እና ገንደ ጋራ ተካሂዷል። በዛሬው ዕለት በአስተዳደሩ ህንፃ ፊት ለፊት ተገኝተው ተቃውሞ እና ጥያቄ ያቀረቡት የኅብረተሰቡ አካላት «ችግር ፈጣሪዎች ተጠያቂ ይሁኑ፣ አስተዳደሩ በየጊዜው ለሚፈጠረው ግጭት ዘላቂ መፍትሄ ይስጥ» የሚሉ እና ሌሎች ጥያቄዎችም አቅርበዋል።

መሳይ ተክሉ 
ኂሩት መለሰ 
ማንተጋፍቶት ስለሺ