ሰላማዊ ሰልፍ በአዲስ አበባ
እሑድ፣ ነሐሴ 2 2013ማስታወቂያ
በአዲስ አበባ ዛሬ እሁድ ህወሓትን እና የኢትዮጵያ መንግሥት ባለሥልጣናት ምዕራባውያን ያደርጉታል የሚሉትን ጣልቃ ገብነት የሚቃወም ሰልፍ ተደርጓል። በሰልፉ የአዲስ አበባ ምክትል ከንቲባ አዳነች አቤቤ እና የኦሮሚያ ክልል ፕሬዝዳንት ሽመልስ አብዲሳ ንግግር አድርገዋል። ከአዲስ አበባ እና በዙሪያዋ ከሚገኙ የኦሮሚያ ክልል ልዩ ዞኖች የተውጣጡ ሰልፈኞች ተሳትፈዋል። እንዲህ አይነት ሰላማዊ ሰልፎች አዲስ አበባን ጨምሮ በተለያዩ የኢትዮጵያ ከተሞች ሲካሔዱ ቆይተዋል።
ስዩም ጌቱ
እሸቴ በቀለ