ሰላማዊ ሰልፍ በአዲስ አበባ
ሐሙስ፣ ሐምሌ 15 2013ማስታወቂያ
ሕወሓትን የሚቃወም እና የህዳሴውን ግድብ ሁለተኛ ዙር ሙሌት የሚደግፍ ሰልፍ ዛሬ በአዲስ አበባ ከተማ ተካሄደ።በአዲስ አበባ ከተማ የሴቶች እና ወጣቶች ማሕበራት ጥምረት በተጠራው በዚሁ ሰላማዊ ሰልፍ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በአሸባሪነት የፈረጀውን ሕወሃትን የሚቃወሙ እና በኢትዮጵያ የውስጥ ጉዳይ ጣልቃ የሚገቡ የውጭ መንግስታት እና ከፋፋይ ሃሳቦችን የሚነቅፉ መልዕክቶች ተስተጋብተዋል። ሁለተኛው ዙር የህዳሴ ግድብ ሙሌት በስኬት መጠናቀቁን በተመለከተ የደስታ መግለጫ መልዕክቶችን ያነገቡ ሰልፈኞችም ታይተዋል። የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ አዳነች አቤቤ ሰልፉን “ለአገር ክብርና ሉዓላዊነት የመቆም ፅኑ ፍላጎት” ብለውታል። የአዲስ አበባው ዘጋቢያችን ስዩም ጌቱ በሰልፉ ስነስረዓት ላይ ታድሞ ተከታዩን ዘገባ ልኮልናል።
ስዩም ጌቱ
ታምራት ዲንሳ
ኂሩት መለሰ