ሰላማዊ ሰልፍ በሀዋሳ
ሐሙስ፣ የካቲት 14 2011ማስታወቂያ
ዛሬ ሀዋሳ ውስጥ በብዙ ሺህ የሚቆጠሩ ነዋሪዎች የሲዳማ ህዝብ ያቀረበው የክልል መዋቅር ጥያቄ በአፋጣኝ ተግባራዊ ይሁንልን ሲሉ በሰላማዊ ሰልፍ ጠየቁ፡፡ ከሀዋሳና ከሲዳማ ዞን አጎራባች ወረዳዎች በመነሳት በከተማዋ ስታዲየም የተሰበሰቡት ሰልፈኞች ለክልላዊ መዋቅር ጥያቄው ምላሽ ይሰጣል የተባለው ህዝበ ውሳኔ በአፋጣኝ ገቢራዊ እንዲሆን ጠይቀዋል፡፡ ዛሬ ከተካሄደው ሠልፍ ጋር ተያይዞ ሁከትና ግርግር ሊነሳ ይችላል በሚል ሥጋት በከተማዋ የሚገኙ ትምህርት ቤቶች እና የንግድ ተቋማት በከፊል ተዘግተው ውለዋል፡፡ ይሁንእንጂ የሰልፉ መረሃግብር በሰላማዊ መንገድ መጠናቀቁን ነው የተነገረው ፡፡ ሰላማዊ ሰልፉን የተከታተለው የሀዋሳው ወኪላችን ሸዋንግዛው ወጋየሁ ተከታዩን ዘግቧል፡፡
ሸዋንግዛው ወጋየሁ
ኂሩት መለሰ
ሸዋዬ ለገሠ