«ረሃብ የሀገሪቱ ስጋት አይደለም»
ረቡዕ፣ ታኅሣሥ 14 2013ማስታወቂያ
«ኢንተርናሽናል ረስኪዩ ኮሚቴ » የተባለ ግብረ ሰናይ ድርጅትት በኢትዮጵያ ውስጥ የተከሰተው የአንበጣ መንጋ እና የትግራይ ክልል ቀውስ በርካታ ዜጎችን ለረሀብና ለአስቸኳይ ርዳታ ፈላጊነት ሊዳርጋቸው ይችላል ሲል አሳሰበ። የኮሮና ወረርሽኝ የፈጠረው የኢኮኖሚ መቀዛቀዝንም ለዚህ ማስጠንቀቂያው በተጨማሪ ምክንያትነት የጠቀሰው ይሄው ድርጅት መንግሥት ሁሉን አቀፍ ድጋፍ እንዲያደርግ ጠይቋል። የብሔራዊ ሥጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን በበኩሉ የሰብዓዊ እርዳታ ፈላጊዎች እና የዕለት ድጋፍ የሚያስፈልጋቸው ዜጎች ቁጥር ሊጨምር እንደሚችል ቢገመትም ረሀብ ግን የሀገሪቱ ሥጋት ሊሆን እንደማይችል ተናግራል። ሰሎሞን ሙጬ ከአዲስ አበባ ዝርዝሩን ልኮልናል።
ሰሎሞን ሙጬ
ኂሩት መለሰ
ሸዋዬ ለገሠ