ሦስት የፖለቲካ ፓርቲዎች ሊዋሐዱ ነው
ሐሙስ፣ ታኅሣሥ 18 2011ማስታወቂያ
ሦስት የኢትዮጵያ የፖለቲካ ፓርቲዎች ለውሕደት ዝግጅት ላይ ነን እያሉ ነው። ተዋሕደን ጠንካራ ፓርቲ ለመመስረት ተቃርበናል ያሉት ሰማያዊ ፓርቲ፣ የኢትዮጵያ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ኢዴፓ)፤ አርበኞች ግንቦት ሰባት ንቅናቄ ናቸው። የፖለቲካ አራማጆች፡ ከእስር የተፈቱ ሰዎችና ከውጭ የተመለሱ ታዋቂ ኢትዮጵያዊያን አዲስ ይመሰረታል ተብሎ በሚጠበቀው ፓርቲ ውስጥ ይሳተፋሉ ተብሏል። የሚመሰረተው የፖለቲካ ፓርቲ የኢትዮጵያዊያንን የጋራ እሴቶች ፡ ተስፋዎች እና ማህበራዊ ፍትህን የሚያቀነቅን እንደሆነ ታውቋል፡፡በውሕደቱ በመሰረታዊነት ስምምነት ላይ የተደረሰ ሲሆን የሚዋሃዱት ፓርቲዎች ጠቅላላ ጉባኤዎች በተናጠል ሲያጸድቁት ህግንና አሰራርን ተከትሎ ይፈጸማል። ሰለሞን ሙጬ ተጨማሪ ዘገባ አለው
ሰለሞን ሙጬ
እሸቴ በቀለ
ነጋሽ መሐመድ