1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

"ሥቃይ እና መከራችን እየበዛ ነው" በሳዑዲ አረቢያ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን

ሰኞ፣ ሐምሌ 19 2013

በሳዑዲ አረቢያ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን "ሥቃያችን፣ እንግልታችን እና መከራችን እየበዛ ነው" እያሉ ነው። አንዲት ወጣት "ሕፃናት እየሞቱብን ነው፤ እህት ወንድሞቻችን እየተሰቃዩብን ነው። ነፍሰ ጡር ሴቶች እየተሰቃዩ ነው" ብላለች። አገሪቱ የስደተኞች ሕጓን ካሻሻለች በኋላ ጉዳዩ መወሳሰቡን በሳዑዲ አረቢያ የኢትዮጵያ አምባሳደር ሌንጮ ባቲ ተናግረዋል

https://p.dw.com/p/3y54j
Karte Horn von Afrika Golfstaaten EN

በሳዑዲ አረቢያ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ሮሮ

በሳዑዲ አረቢያ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ማንነታቸው እየተለየ ሞት እስር ግፍና መከራ እየተፈፀመባቸው መሆኑ ተገለፀ:: ኢትዮጵያኑ እንደሚሉት የመኖሪያ ፈቃድ ያላቸው ጭምር ቤታቸው እየተሰበረ ከነልጆቻቸው ወደእስር ቤት በመወርወር ላይ ናቸው:: በሳዑዲ አረቢያ የኢትዮጵያ አምባሳደር ሌንጮ ባቲ ችግሩ እጅግ ውስብስብ እንደሆነና ዜጎችን ወደሃገራቸው የመመለስ ስራ ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት አመልክተዋል::

ታሪኩ ኃይሉ 

ሸዋዬ ለገሰ