ሠይፉ ፋንታሁን በዶይቸ ቬለ-ቃለ-መጠይቅ
ማክሰኞ፣ ግንቦት 20 2011ማስታወቂያ
ዶይቸቬለ በየዓመቱ የሚዘጋጀው ዓለም አቀፍ የመገናኛ ብዙኃን መድረክ ከትናንት ጀምሮ በመካሄድ ላይ ነው። እዚህ ቦን ከተማ ዘንድሮ ለ12ኛ ጊዜ በተዘጋጀው በዚህ መድረክ ከኢትዮጵያ በርከት ያሉ ተጋባዦች ተገኝተዋል። በመገናኛ ብዙኃን ዘርፍ የሚሠሩትም ከዶይቼ ቬለ የአማርኛ ክፍል ባልደረቦች ጋር ቢሮችን በመገኘት ተወያይተዋል። ከእነሱ መካከል ከአዲስ አበባው ኢትዮ ኤፍ ኤም የመጣው አርቲስት ሠይፉ ፋንታሁን አንዱ ነው። የዶይቼ ቬለን የቀጥታ ስርጭት አዲስ አበባ ላይ የሚያስተላልፈው ኢትዮ ኤፍ ኤም መሥራቾች አንዱ ሠይፉ ፋንታሁን ከማንተጋፍቶት ስለሺ ቃለ-መጠይቅ አድርጓል።
ማንተጋፍቶት ስለሺ
ሸዋዬ ለገሰ