ሞት እና የኢትዮጵያ ዲያስፖራ ፈተና
ሐሙስ፣ የካቲት 28 2011ማስታወቂያ
ከሀገር ከወገን እና ከሚያውቁት አካባቢ በተለያዩ ምክንያቶች እና አጋጣሚዎች ርቆ በውጪው ዓለም የሚኖረው ወገን ከመልካም ገጠመኙ ጎን ለጎን ዕለት ዕለት የሚሳቀቅባቸው እና የሚያዝንባቸው አልፎ ተርፎም ከሀገር የራቀበትን ቀን የሚያማርር የሚረግምባቸውን ድንገቶች ሊጋፈጥ ይገደዳል። ሀገር ቤት ሳለ በቤተሰብ ኃላፊነት የሚሸፈነው የማኅበረሰብ ግንኙነት በውጭው ዓለም ብቻውን መቋቋም እና መጋፈጥ ይኖርበታል። የዕለቱ የባህል መሰናዶ በውጭው ዓለም ኢትዮጵያውያን እርስ በርስ ለመደጋገፍ እና ለመረዳዳት ሊጠቀሙባቸው ከሚገቡ ማኅበራዊ ተቋማት አንዱ ስለሆነው ስለዕድር ተሞክሮዎችን ተንተርሶ የሚለን ይኖረዋል። ዝግጅቱን ከለንደን ሃና ደምሴ አጠናቅራዋለች።
ሃና ደምሴ
ሸዋዬ ለገሠ
ተስፋለም ወልደየስ