1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ምዕራብ ጎንደር ዞን 4ሺህ ይህል ተፈናቃዮች ተመለሱ

ማክሰኞ፣ ግንቦት 23 2014

በአማራ ክልል ምዕራብ ጎንደር ዞን በነበሩ የፀጥታ ችግሮች ተፈናቅለው ወደ ሌሎች አካባቢዎች ተፈናቅለው የነበሩ 4ሺህ ያህል የመተማና የአገር አድን ጨቆ ወረዳ ተፈናቃዮች ወደ ቀያቸው እየተመለሱ መሆናቸውን የአካባቢው አመራር ዐስታወቁ፣ ተፈናቃዮች በበኩላቸው ወደ ቦታቸው መመለሳቸው ቢያስደስታቸውም አስፈላጊ ቁሳቁሶች እንዳልተሟሉላቸው ይናገራሉ።

https://p.dw.com/p/4C6WO
Äthiopien IDPs in der Region Amhara
ምስል Alemenw Mekonnen/DW

በክልሉ ከ2 ሚሊዮን 300ሺህ በላይ ተፈናቃይ አለ

በአማራ ክልል ምዕራብ ጎንደር ዞን በነበሩ የፀጥታ ችግሮች ተፈናቅለው ወደ ሌሎች አካባቢዎች ተፈናቅለው የነበሩ 4ሺህ ያህል የመተማና የአገር አድን ጨቆ ወረዳ ተፈናቃዮች ወደ ቀያቸው እየተመለሱ መሆናቸውን የአካባቢው አመራር ዐስታወቁ፣ ተፈናቃዮች በበኩላቸው ወደ ቦታቸው መመለሳቸው ቢያስደስታቸውም አስፈላጊ ቁሳቁሶች እንዳልተሟሉላቸው ይናገራሉ። የዞኑ መንግስት ግን ተመላሾችን ለማገዝ የተቻለው ሁሉ ጥረት ይደረጋል ብሏል። 

በምዕራብ ጎንደር ዞን በተለያዩ ወረዳዎች በነበሩ የአማራና ቅማንት ግጭቶች፣ እንዲሁም ከህወሓት ጋር በነበሩ ጦርነቶች በነበሩ አለመረጋጋቶች ምክንያት በርካታ ሰዎች ከቀያቸው ተፈናቅለው ቆይተዋል፡፡ ይሁን እንጂ አሁን አንፃራዊ ሰላም በአካበባው በመፈጠሩ 2ሺህ 700 ተፈናቃዮች ወደ ቀያቸው እየተመለሱ መሆናቸውን የዞኑ አደጋ መከላከልና ምግብ ዋስትና ጽ/ቤት ተጠሪ ኃላፊ አቶ አበባው በዛብህ ለዶይቼ ቬሌ ተናግረዋል፡፡ የዞኑ የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ ኃላፊ አቶ ፋንታሁን ቢሆነኝም ተፈናቃዮች እተመለሱ መሆናቸውን አረጋግጠዋል፡፡ 
የመተማ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ማሩ ሙሉጌታ በበኩላቸው፣ በወረዳው ከ8 ወራት በፊት በነበሩ የሰላም መደፍረስ ምክንያት ተፈናቅለው ከነበሩ ነዋሪዎች መካከል 1ሺህ 300 የሚሆኑት ወደ መደበኛ ኑሯቸው እየተመለሱ ነው ብለዋል፡፡ 

አንዳንድ ተፈናቃዮች ወደ ቀያቸውመ መለሳቸው ቢያስደስታቸውም አለመረጋጋት ሊኖር ይችል የሚል ስጋት አድሮባቸዋል፣ የእርሻ መሳሪያዎች፣ የመኖሪያ ቤቶች አለመስተካከል እንዳለባቸውም ገልፀዋል፡፡ የመተማ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶማሩ ግን አስተማማኝ ሰላም መኖሩንና መታገዝ የሚገባቸው ነገሮችም ተለይተዋል ብለዋል፡፡ 
የዞኑ አደጋ መከላከልና ምግብ ዋስትና ጽ/ቤት ተጠሪ ኃላፊ አቶ አበባው በዛብህ በበኩላቸው ዋናው ስራ ተፈናቃዮችን መመለስ ሲሆን የቀሩ ጉዳዮች ከበላይ አካል ጋር በመነጋገር የሚፈቱ ይሆናሉ ነው ያሉት፡፡ 

በአማራ ክልል ከ2 ሚሊዮን 300ሺህ በላይ ተፈናቃይ ሲኖር ከ9 ሚሊዮን በላይ የሚሆን ደግሞ ቋሚ እርዳታ ፈላጊ እንደሚኖር ከክልሉ አደጋ መከላከል፣ ምግብ ዋስትና ማስተባበሪያና ልዩ ዳጋፍ ከሚሹ ኮሚሽን ያገኘነው መረጃ ያሳያል፡፡ 

ዓለምነው መኮንን

ማንተጋፍቶት ስለሺ

እሸቴ በቀለ