ምዕራብ ወለጋ አዲስ ግጭት
ማክሰኞ፣ ጥቅምት 23 2014ማስታወቂያ
በምዕራብ ወለጋ ዞን ቤጊና ቆንዳላ በተባሉ ወረዳዎች በሸመቁ ታጣቂዎችና በኢትዮጵያ መከላከያ ጦር መካከል ባለፈዉ ቅዳሜ በተደረገ ግጭት በርካታ ሰዎች መገደላቸዉንና በሺሕ የሚቆጠሩ መፈናቀላቸዉን የአካባቢዉ ነዋሪዎች አስታወቁ። ዉጊያዉን ሸሽተዉ በኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የገቡ ተፈናቃዮች እንደሚሉት በግጭቱ ቁጥሩን በትክክል የማያዉቁት የአካባቢዉ ነዋሪ ተገድሏል። ከ3ሺሕ የሚበልጥ ሕዝብ ተፈናቅሏል፣ የስልክና የኢንተርኔት አገልግሎትም የለም። የበኒሻንጉል ጉሙዝ የአደጋ ሥጋት ሥራ አመራር ኮሚሽንም ከሁለቱ ወረዳዎች የሸሹ ከ3ሺሕ በላይ ተፈናቃዮች መመዝገቡን አረጋግጧል።
ነጋሳ ደሳለኝ
ነጋሽ መሐመድ
ማንተጋፍቶት ስለሺ