1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ምክር ቤቱ 122 ቢሊዮን ብር ተጨማሪ በጀት አፀደቀ

ዓርብ፣ ጥር 20 2014

ምክር ቤቱ ዛሬ ካፀደቀዉ ተጨማሪ በጀት 90 ቢሊዮኑ ለጦር ኃይል፣ 8 ቢሊዮኑ ለችግረኞች የምግብ ዕሕል መግዢያ፣ 8 ቢሊዮኑ ለመጠባበቂያ እና 5 ቢሊዮኑ በጦርነት ለወደሙ የመሠረተ ልማት አዉታሮች መጠገኛ ይዉላል ተብሏል

https://p.dw.com/p/46E1Z
Äthiopien Premierminister Abiy Ahmed Parlament
ምስል Yohannes Gebireegziabher/DW

ከተጨማሪዉ በጀት 90 ቢሊዮን ብሩ ለጦር ኃይል የሚዉል ነዉ

የኢትዮጵያ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ለፌዴራል መንግሥት የ2014 ወጪ  122 ቢሊዮን ብር ተጨማሪ በጀት አፀደቀ።ምክር ቤቱ ዛሬ ካፀደቀዉ ተጨማሪ በጀት 90 ቢሊዮኑ ለጦር ኃይል፣ 8 ቢሊዮኑ ለችግረኞች የምግብ ዕሕል መግዢያ፣ 8 ቢሊዮኑ ለመጠባበቂያ እና 5 ቢሊዮኑ በጦርነት ለወደሙ የመሠረተ ልማት አዉታሮች መጠገኛ ይዉላል ተብሏል።ምክር ቤቱ ከዚሕ ቀደም ለ12014 የ561.7 ቢሊዮን ብር በጀት አፅድቆ ነበር።አሁን ተጨማሪ በጀት ያስፈለገዉ ጦርነት ባሳደረዉ ጫና ምክንያት እንደሆነ የገንዘብ ሚንስቴር ከወራት በፊት አስታዉቆ ነበር።ተጨማሪዉ በጀት ከሐገር ዉስጥ ብድር የሚሸፈን እንደሆነ ተነግሯል።

ሰለሞን ሙጬ 

ነጋሽ መሐመድ

እሸቴ በቀለ