1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ምርጫው በአዲስ አበባ

ሰኞ፣ ሰኔ 14 2013

ስድተኛው አገር አቀፍ ምርጫ ከንጋቱ 12 ሰዓት ጀምሮ በአዲስ አበባ ከተማ ሲከናወን ውሏል። በሂደቱ ምርጫው በተቀመጠለት ሰዓት አለመጀመር እና ረጃጅም ሰልፎች በምርጫ ጣቢያዎች ላይ በስፋት ተስተውሏል።

https://p.dw.com/p/3vIGk
Äthiopien | Parlamentswahl | Adanech Abebe
ምስል Solomon Muchie/DW

ከጠዋቱ 12 ሰዓት ተጀመረ

ስድተኛው አገር አቀፍ ምርጫ ከንጋቱ 12 ሰዓት ጀምሮ በአዲስ አበባ ከተማ ሲከናወን ውሏል። በሂደቱ ምርጫው በተቀመጠለት ሰዓት አለመጀመር እና ረጃጅም ሰልፎች በምርጫ ጣቢያዎች ላይ በስፋት ተስተውሏል።  የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ብርቱካን ሚዴቅሳ እኩለ ቀን ላይ በሰጡት መግለጫ የምርጫ ሂደቱ ሰላማዊ ሆኖ ሲከናወን መዋሉን ገልፀዋል። ሆኖም የቁሳቁስ እጥረቶች ብዙ ቦታዎች ላይ እንዳጋጠሙ ገልፀው በተለይ አሶሳ ላይ ችግሩ ጎልቶ መታየቱን ገልፀዋል።
በሌላ በኩል በአማራ እና ደቡብ ክልሎች እንዲሁም በከፊል በአፋር ክልል ሥጋት የሚፈጥሩ ያሏቸው ችግሮች መከሰታቸውን ተናግረዋል። ይህም የፖለቲካ ፓርቲ ወኪሎች ከቦታ ቦታ መንቀሳቀስ አለምቻል፣ድብደባ እየተፈፀመባቸው እንደሆነ ፣ ባጅ እየተቀሙ እንደሆነ እና ወደ ምርጫ ጣቢያ ሊጠጉ የማይችሉበት ሁኔታ ከብልፅግና በስተቀር ብዙ ፓርቲዎች አቤት ማላቸውን ተናግረዋል።

ሰሎሞን ሙጬ

ሸዋዬ ለገሠ

ኂሩት መለሰ