1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

«ምርጫ ከማካሄድ የሚያቆመን ምድራዊ ኃይል የለም» የትግራይ ክልል ም/ቤት

ማክሰኞ፣ ሐምሌ 28 2012

የትግራይ ክልል ምክርቤት በፌደሬሽን ምክርቤት የቀረበለትን በክልሉ የምርጫ እንቅስቃሴ እንዲቆም የሚያሳስብ ደብዳቤ እንደማይቀበለው አስታወቀ፡፡ የክልሉ ምክር ቤት ትላንት ለፌደሬሽን ምክርቤት በሰጠው ምላሽ በክልሉ ሊካሄድ በእንቅስቃሴ ላይ ያለው ምርጫ የትግራይ ህዝብን ፍላጎት መሰረት ያደረገ ነው ብሏል።

https://p.dw.com/p/3gP6u
Äthiopien Tagung der Volksbefreiungsfront von Tigray
ምስል DW/M. Haileselassie

«የፌዴሬሽን ምክር ቤት ማስጠንቀቂያን አንቀበልም» የትግራይ ክልል

የትግራይ ክልል ምክርቤት በፌደሬሽን ምክርቤት የቀረበለትን በክልሉ የምርጫ እንቅስቃሴ እንዲቆም የሚያሳስብ ደብዳቤ እንደማይቀበለው አስታወቀ፡፡ የክልሉ ምክር ቤት ትላንት ለፌደሬሽን ምክርቤት በሰጠው ምላሽ በክልሉ ሊካሄድ በእንቅስቃሴ ላይ ያለው ምርጫ የትግራይ ህዝብን ፍላጎት መሰረት ያደረገ ነው ብሏል። በክልል ደረጃ ምርጫውን ማካሄድ ሕገ መንግስታዊ መሆኑን እና ይህን ሊያቆም የሚችል ኃይል እንደሌለም  ገልጿል፡፡

ሚሊዮን ኃይለስላሴ

ነጋሽ መሐመድ