1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ምርጫ ቦርድ ስለ ሲዳማ ህዝበ ውሳኔ ዝግጅት

ሐሙስ፣ ሐምሌ 11 2011

በደቡብ ብሔር ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች ክልላዊ መንግሥት ስር የሚገኘው የሲዳማ ዞን ራሱን በራሱ የሚያስተዳድር ክልል እንዲሆን የዞኑ ምክር ቤት ከወሰነ ዛሬ አንድ ዓመት ደፈነ። ውሳኔውን መሠረት በማድረግ የደቡብ ክልሉ የዞኑን የክልልነት ጥያቄ ለመወሰን ሕዝበ ውሳኔ እንዲደራጅለት ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ጥያቄ ማቅረቡም ይታወሳል።

https://p.dw.com/p/3MHRK
Äthiopien Wahlen 2015
ምስል DW/E. Bekele

ብሔራዊ የምርጫ ቦርድ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሐምሌ 10 2011 ባወጣው መግለጫ «በሕግ መንግሥቱ የተጠቀሰው የጊዜ ገደብ ሊጠናቀቅ በቀሩት አምስት ወራት ውስጥ ሕዝበ ውሳኔውን ለማከናወን የመጀመሪያ ደረጃ ዝግጅት» በማድረግ ላይ መሆኑን አስታውቋል። ስለ ዝግጅቱ እና ሂደቱ የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ ምክትል ሰብሳቢ አቶ ውብሸት አየለን የአዲስ አበባው ዘጋቢያችን ጌታቸው ተድላ ኃይለ ጊዮርጊስ አነጋግሯቸዋል።  

ጌታቸው ተድላ ኃይለ ጊዮርጊስ

ኂሩት መለሰ

አዜብ ታደሰ