ምርጫ በደብረ-ብርሃን
ሰኞ፣ ሰኔ 14 2013ማስታወቂያ
በደብረ ብርሃን የምርጫ ክልል የተመዘገቡ ከ73 ሺሕ በላይ ድምፅ ሰጪዎች የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እና የክልል ምክር ቤት ተወካዮቻቸውን ሲመርጡ ውለዋል። በከተማዋ የሚገኘው የዶይቼ ቬለ ዘጋቢ ያነጋገራቸው መራጮች የሚመረጠው መንግሥት ሊሠራ ይገባል የሚሏቸው በርካታ ጉዳዮች አሉ። ሰላም እና ጸጥታ በበርካቶች ተደጋግመው ከሚነሱ ጉዳዮች አንዱ ነው።
በደብረ ብርሃ ከተማ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መቀመጫዎች ብልፅግና ፓርቲ፣ የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ-ፍትህ ፓርቲ፣ የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ፣ እናት ፓርቲ፣ ኅብር ኢትዮጵያ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ እና የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት ስድስት እጩዎች አቅርበዋል። ከስድስቱ አንዷ ብቻ እንስት ናቸው። ለአማራ ክልል ምክር ቤት ደግሞ ከኅብር ኢትዮጵያ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ በቀር አምስቱ ፓርቲዎች ሁለት ሁለት እጩዎች ከተማዋን ለሚወክሉ መቀመጫዎች ያወዳድራሉ።
እሸቴ በቀለ
ማንተጋፍቶት ስለሺ
ሸዋዬ ለገሰ
ኂሩት መለሰ